የጌታ መንፈስ
Yegieta Menfes
2011 · ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የጌታ መንፈስ በላዬ ወርዶ(፫x)
አጥፋው ይለኛል ሰይፉን አሲዞ(፫x)
የጌታ መንፈስ በላዬ ወርዶ(፫x)
አጥፋው ይለኛል ሰይፉን አሲዞ(፫x)
አሃሃሃ ጠላቴ ሊያመልጥ ለምን ይሞክራል
የእግዚአብሔር እሳት ዙሪያውን ከቦታል
ኤልያስ የእስራኤል ነው ተራው የእኔ ሆኗል
እግዚአብሔር ቅባቱን በእኔ ላይ ለቆታል
የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው(፪x)
ለታሰሩት መፈታት ላዘኑት መጽናናት እናገር ዘንድ ልኮኛል
ጌታ መንፈሱ በእኔ ላይ ነው
እግዚአብሔር የቀባኝ ሰልፍን ያስተማረኝ
ጐልያድን እንድመታ ያንን ያዝጋጀኝ
ልባቹህ አይውደቅ በጩኸቱ ብርታት
ተመቶ ይወድቃል በአምላኬ ጉልበት
የጨለማ ስልጣን ጥቃት በዝቶበታል
የእኔ ነው ያለውን ለቆ ሲሸሽ ታይቷል
ፓውሎስ ጴጥሮስ የሉም እኛን ተክተዋል
ለእኔ ለአንተ ለአንቺ አደራ ሰጥተዋል
አዝማች · Chorus
የጌታ መንፈስ በላዬ ወርዶ(፫x)
አጥፋው ይለኛል ሰይፉን አሲዞ(፫x)
የጌታ መንፈስ በላዬ ወርዶ(፫x)
አጥፋው ይለኛል ሰይፉን አሲዞ(፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ