Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በቃልህ

Beqaleh

2011 · ትራክ 3 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አልቅበዘበዝም ከእንግዲህማ

በሥጋ አልወጣም ከእንግዲህማ

ግን በቃልህ መረቤን/ነገሬን እጥላለሁ

የተሻለ ያን ጊዜ አገኛለሁ (፪x)

እንደ ቃልህ መረቤን እጥላለሁ

የተሻለ በቃልህ/በጌታ አገኛለሁ (፪x)

የድካም ሌሊት ሆኖ ሌሊቱ

ለካ ይፈተናል ሰውም ትዕግሥቱ

የራሴን ጥረት ሁሉ ጥሬያለሁ

ታንኳ መረቤ ባየው ባዶ ነው

አሁንማ በቃልህ መረቤን እጥላለሁ

አሁንም ሙግቴን ሁሉ እተዋለሁ

አሁንማ የአንተ ሃሳብ ይሻላል እላለሁ

አሁንማ አየሁት የእኔማ ከንቱ ነው

መቼ ከጉድጓድ ጋር የይሳቅ ነገሩ

የአምላኩ ቃልኪዳን ከእርሱ ጋር መኖሩ

በስጥና በኤሴቅ ሲያጋፉት ቢያያቸው

ርሆቦት ደረሰ ሁሉን ትቶላቸው

በረከቴ ብለው ጉድጓዱን ለሚያዩ

አይደለም አልኳቸው ከላይ ነው ጉዳዩ

ሰው ቆፍሮ ያመጣው ይነቅፋል ይደርቃል

በቃልህ የጀመረ እርሱ መቼ ያፍራል

አልቅበዘበዝም ከእንግዲህማ

በሥጋ አልወጣም ከእንግዲህማ

ግን በቃልህ መረቤን/ነገሬን እጥላለሁ

የተሻለ ያን ጊዜ አገኛለሁ (፪x)

እንደ ቃልህ መረቤን እጥላለሁ

የተሻለ በቃልህ/በጌታ አገኛለሁ (፪x)

ስለ እኔ አውቃለሁ ሃሳቢ አልሻም

ውጥኔ በእጄ አለው መድረሻ

ብዬ ፎክሬ በራሴ ትግል

ኋላ ነቃሁኝ ስደክም ስዝል

አሁንማ ፈቃድህ ይሆን እላለሁ

አሁንማ ከአንተ የሆነውን እሻለሁ

አሁንማ . (1) . መስገን እንዳይሆን እጣዬ

አሁንማ እንደቃልህ መረብ ኑሮዬ

አልቅበዘበዝም ከእንግዲህማ

በሥጋ አልወጣም ከእንግዲህማ

ግን በቃልህ መረቤን/ነገሬን እጥላለሁ

የተሻለ ያን ጊዜ አገኛለሁ (፪x)

መቼ ከጉድጓድ ጋር የይሳቅ ነገሩ

የአምላኩ ቃልኪዳን ከእርሱ ጋር መኖሩ

በስጥና በኤሴቅ ሲያጋፉት ቢያያቸው

ርሆቦት ደረሰ ሁሉን ትቶላቸው

በረከቴ ብለው ጉድጓዱን ለሚያዩ

አይደለም አልኳቸው ከላይ ነው ጉዳዩ

ሰው ቆፍሮ ያመጣው ይነቅፋል ይደርቃል

በቃልህ የጀመረ እርሱ መቼ ያፍራል

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ