ዘመን መጣልኝ
Zemen Metalegn
2011 · ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክረምት አለፈ ጐርፎ አልፎ ሄደ
በለስ ጐመራ ወይኑም አበበ
ዘመን ተሰማ ለፍጥረት ሁሉ
ምህረቱ በዝቷል እስቲ እልል በሉ
አዝማች · Chorus
ዘመን መጣልኝ ዘመን
ዘመን መጣልኝ ለእኔማ
የዕልልታዬ ድምጽ ሊሰማ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ከቅጥሬ ኋላ እርሱ ቆሞልኝ
እዚህ ያደረሰኝ ጉልበት ሆኖልኝ
እንዲህ ያደረገ ያ መድሃኒቴ
ዘመን ማጣልን ሰምቶ ጩኸቴን(፪x)
አዝማች · Chorus
ዘመን መጣልኝ ዘመን
ዘመን መጣልኝ ለእኔማ
የዕልልታዬ ድምጽ ሊሰማ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የዕልልታዬ ድምጽ ሊሰማ የዕልልታዬ (፬x)
መንጊያውን ስከተል ከኋላ ኋላ
ምኞቴ ሃሳቤ ነበረ ሌላ
ፍቅሩ ወደቀ ከእረኛው ላይ
ንጉሥ አደረገኝ የለበት ከልካይ
አዝማች · Chorus
ዘመን መጣልኝ ዘመን
ዘመን መጣልኝ ለእኔማ
የዕልልታዬ ድምጽ ሊሰማ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከቅጥሬ ኋላ እርሱ ቆሞልኝ
እዚህ ያደረሰኝ ጉልበት ሆኖልኝ
እዘምራለሁ ሆኜ አለቱ ላይ
የዝማሬ ድምጽ ይግባልኝ ሰማይ(፪x)
አዝማች · Chorus
ዘመን መጣልኝ ዘመን
ዘመን መጣልኝ ለእኔማ
የዕልልታዬ ድምጽ ሊሰማ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
የዕልልታዬ ድምጽ ሊሰማ የዕልልታዬ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ