Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ባለ ግርማ

Bale Germa

2011 · ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የእኔ ጌታ በዙፋኑ ያለው

ትልቅ ነው እኩያ የሌለው (፪x)

ባለ ግርማ ነዉ ፣ ባለ ግርማ ነዉ (፬x)

በዙፋኑ ላይ ይተቀመጠው

የአባቶቼ አምላክ እርሱ ትልቅ ነዉ (፪x)

እርሱ ትልቅ ነው እርሱ ትልቅ ነው

እኩያ የለው አምሳያ የለው

ብዙዎች ነበሩ አንቱ የተባሉ

በአስቀመጡት ታሪክ ዛሬ ይወሳሉ

ትዝታቸው ቀረ ነበሩ ተብለው

የትላንት ደማቆች ዛሬ ታሪክ ሆነው

(የእኔ ጌታማ) ዝናው አይቀዘቅዝ

(የእኔ ጌታማ) ስራው የማይነቅዝ

(የእኔ ጌታማ) በክብር ይኖራል

(የእኔ ጌታማ) ሁሉንም ይገዛል

ሃያል አምላክ ነዉ ሃያል አምላክ (፪x) ነዉ

ታላቅ አምላክ ነዉ ታላቅ አምላክ (፪x) ነዉ

ሃያል ነዉ ከሃያላን በላይ አምላኬ የበላይ

ብርቱ ነው ከብርቱዎች በላይ አምላኬ የበላይ

ባለ ግርማ ነዉ ፣ ባለ ግርማ ነዉ (፬x)

በዙፋኑ ላይ ይተቀመጠው

የአባቶቼ አምላክ እርሱ ትልቅ ነዉ (፪x)

ጽኑሃን ሃያላን የምድር ነገሥታት

መንግሥታቸው ሲወድቅ ባላሰቡት ሰዓት

ግብራቸው ሲዋረድ ሲሻር ሹመታቸው

ትዝታን ታቅፈው ሁሉም ሲከዳቸው

(የእኔ ጌታማ) መንግሥቱ ዘለዓለም

(የእኔ ጌታማ) የሚተካው የለም

(የእኔ ጌታማ) የሚመስለው ማነው

(የእኔ ጌታማ) የክብር ንጉሥ ነው

ሃያል አምላክ ነዉ ሃያል አምላክ (፪x) ነዉ

ታላቅ አምላክ ነዉ ታላቅ አምላክ (፪x) ነዉ

ሃያል ነዉ ከሃያላን በላይ አምላኬ የበላይ

ብርቱ ነው ከብርቱዎች በላይ አምላኬ የበላይ

ሃያል ነዉ ሃያል

ሃያል ነዉ ሃያል አምላክ ነዉ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ