አንተን አንተን
Anten Anten
2011 · ትራክ 10 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንተን አንተን ይላል ልቤ (፬x)
ብር ወርቅም አይደለም ረሃቤ
ክብርህን ሳየው ነው ጥጋቤ
ከሁሉ የምትበልጥ ምርጫዬ
የነፍሴ እርካታ ጌታዬ
አንተን አንተን ይላል ልቤ (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰው በልቶ ጠጥቶ ለብሶ ተሽሞንሙኖ
በየአደባባዩ ሚዛን ደፍቶ ቀኑ
ነፍሱ ግን ተራቁታ ከስታና መንምና
ነገሮች ቢሟሉም እርካታ ቢስ ሆና
ለእኔ ግን የውጪው አይደለም
ለእኔ ግን ቀዳሚው ናፍቆቴ
ለእኔ ግን የፊትህ ብርሃን
ለእኔ ግን ክብሬ ነው ድምቀቴ
ለእኔ ግን ቁስ አይተካልኝም
ለእኔ ግን አይሆነኝ እርካታ
ለእኔ ግን ሁሌም አብርሆትህ
ለእኔ ግን የዘመኔ ደስታ
አዝማች · Chorus
አንተን አንተን ይላል ልቤ (፬x)
ብር ወርቅም አይደለም ረሃቤ
ክብርህን ሳየው ነው ጥጋቤ
ከሁሉ የምትበልጥ ምርጫዬ
የነፍሴ እርካታ ጌታዬ
አንተን አንተን ይላል ልቤ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አልናፍቀውም የዚን ዓለም ክብር ዝና
አልናፍቀውም ጠፊ ነው አውቃለሁ ጌታ
አልናፍቀውም አንተን ትቶ መኖር ለአፍታ
አልናፍቀውም ዝርግፍ ጌጤ እኮ ነህ ጌታ
ኢየሱስ በየትኛውም ስፍራ
ኢየሱስ ልኑር ከአንተ ጋራ
ኢየሱስ የሕይወቴ ቁም ነገር
ኢየሱስ ለአንተ ብቻ መኖር
ፊትህ ይብራልኝ በሕይወት ዘመኔ
ከምንም በላይ ክብሬ ነው ለእኔ
በሌለህበት አይሁን ኑሮዬ
መገኘትህ ውስጥ መሰማሪያዬ
ነፍስን ሊያስደስቷት ቢበሉ ቢጠጡ
በሹመኞች ወንበር ደግሞም ቢቀመጡ
የሰው ልጅ ፍላጐት መች በዚህ ይረካል
የያዘውን ጠግቦት ኋላ ሌላ ያምረዋል
ለእኔ ግን የዚች ዓለም መልኳ
ለእኔ ግን ጠፊ ነው ገብቶኛል
ለእኔ ግን ውስጤም አይሳሳለት
ለእኔ ግን ፍቅርህ በልጦብኛል
ለእኔ ግን መኖር ከአንተ ጋራ
ለእኔ ግን ከምንም ይበልጣል
ለእኔ ግን የማያልፍ ምርጫ
ለእኔ ግን አንተ ውለህልኛል
አዝማች · Chorus
አንተን አንተን ይላል ልቤ (፬x)
ብር ወርቅም አይደለም ረሃቤ
ክብርህን ሳየው ነው ጥጋቤ
ከሁሉ የምትበልጥ ምርጫዬ
የነፍሴ እርካታ ጌታዬ
አንተን አንተን ይላል ልቤ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ