Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የፈሰሰ ውኃ

Yefesese Weha

2011 · ትራክ 7 · 5:14 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የፈሰሰ ውኃ በቃ አይታፈስም

ዳግመኛ ሊጠቅም እድልም የለውም

ሰው ተስፋ ሲቆርጥ እንዲህ ይተርታል

የሞተው ሊቀብር አልቅሶ ይወጣል

ጌታ በአንተ ዘንድ የፈሰሰም ውኃ ዳግም ይታፈሳል

ኢየሱስ በአንተ ዘንድ ሞቷል የተባለ በሕይወት ይኖራል

ጌታ በአንተ ዘንድ አይቻልም ሚባል ቃል ከቶ አይገኝም

ኢየሱስ በአንተ ዘንድ የወደቀ ይነሳል ተቆርጦ አይጣልም

አምላኬ ትችላለህ ታሪክን መለወጥ

አምላኬ ትችላለህ መራራውን ማጣፈጥ

ትችላለህ ታሪክን መለወጥ

ትችላለህ መራራውን ማጣፈጥ

(ኢየሱስ) ተስፋ በጠፋበት ፣ (ኢየሱስ) ተስፋ ትሆናለህ

(ኢየሱስ) ታሪክን በታሪክ ፣ (ኢየሱስ) ትለዋውጣለህ

(ኢየሱስ) የጠበቁህ አያፍሩም ፣ (ኢየሱስ) በጽናት የቆዩ

(ኢየሱስ) በረሃው ለምልሞ ፣ (ኢየሱስ) አዲስ ምዕራፍ አዩ

አምላኬ ትችላለህ ታሪክን መለወጥ

አምላኬ ትችላለህ መራራውን ማጣፈጥ

ትችላለህ ታሪክን መለወጥ

ትችላለህ መራራውን ማጣፈጥ

ሞት ጥላውን አቅልጦ___ ፍርሃት ሲነግስ

እምነትን ሊናጠቅ ጠላት ሲገሰግስ

የሕይወት ምዕራፎች ትግላቸው በርትቶ

ተስፋ ያደረጉት ሳይገኝ ዘግይቶ

(ጌታ ያኔማ) ድንገት ዘምበል ስትል ሁሉም ይለወጣል

(ኢየሱስ ያኔማ) የተመሳቀለው በቃልህ ይሰናዳል

(ጌታ ያኔማ) ዘመን ስታመጣ እስከመቼ ላሉ

(ኢየሱስ ያኔማ) በምሥጋና ሆነው ታስበናል ላሉ

ትችላለህ ታሪክን መለወጥ

ትችላለህ መራራውን ማጣፈጥ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ