Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

የልጅነቴ

Yelejenetie

2011 · ትራክ 4 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በምድረ በዳ በጭንቁ ወራት

በልጠህ አገኘህ ከእናትም ከአባት

ልዩ ነህ ለእኔ በአመታቶችህ

ዛሬም ልበልህ ይልጅነቴ

የልጅነቴ አምላክ የልጅነቴ

የልጅነቴ ወዳጅ የልጅነቴ

አንተው ነህ መድሃኒቴ

በአጠገቤ ቆመህ ያበረታኽኝ

ዛሬም አንተው ነህ ለእኔ ያለህልኝ (፪x)

ሲርበኝ አብልተህ ሲጠማኝ አርክተህ

እዚህ አደረስከኝ ወግ ማረግ የሆነኝ ፣ ወግ ማረግ የሆነኝ

በአጠገቤ ቆመህ ያበረታኽኝ

ዛሬም አንተው ነህ ለእኔ ያለህልኝ (፪x)

የጠላቶቼን ቀስት ሰብረህ ጥለህልኝ

በድካሜም ቢሆን ብርታት ሆነህልኝ

ያን ሁላ አልፊአያለሁ በአንተ መድሃኒቴ

ዛሬም ልበልህ የልጅነቴ

የልጅነቴ አምላክ የልጅነቴ

የልጅነቴ ወዳጅ የልጅነቴ

አንተው ነህ መድሃኒቴ

በአጠገቤ ቆመህ ያበረታኽኝ

ዛሬም አንተው ነህ ለእኔ ያለህልኝ (፪x)

አይቼ እንዳልፈራ ሰምቼ እንዳልሰጋ

ተጠነከክልኝ ሆነህ ከእኔ ጋራ ፣ ሆነህ ከእኔ ጋራ

በአጠገቤ ቆመህ ያበረታኽኝ

ዛሬም አንተው ነህ ለእኔ ያለህልኝ (፪x)

ስወድቅ አንስተህ ስጠፋ ፈልገህ

አዳፋዬን ልብሴን በደምህ አንጽተህ ፣ በደምህ አንጽተህ

በአጠገቤ ቆመህ ያበረታኽኝ

ዛሬም አንተው ነህ ለእኔ ያለህልኝ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ