አቤት ውበቱ የሌሊቱ
Abet Wubetu Yelielitu
2005 · ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አቤት ውበቱ አቤት ውበቱ የለሊቱ
ሲገለጥ እውነቱ ውበት አለው ለሊቱ
አቤት ውበቱ አቤት ውበቱ የለሊቱ
ሲታይ እውነቱ ውበት አለው ለሊቱ
የኑሮዬ ለሊት እንዲነጋ የማውቅበት
የሕይወቴ ለሊት ማዳኑን የማይበት (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ዝም ባለው በድቅድቅ ለሊት አጋዥ በሚያሻበት
ግራ ቀኝ እያየሁ ስጣራ ፈልጌ እረዳት
አምላኬ መንፈሴን አንቅቶ አበራልኝ እውነቱን
በከበበኝ ጨለማ መሃል አሳየኝ ምሕረቱን
በሰማይ ያሉ ከዋክብት ሲመሽ እንደሚደምቁት
ዙሪያዬ ሲጨልምብኝ የአምላኬን ማዳን አየሁት (፪x)
አዝማች · Chorus
አቤት ውበቱ አቤት ውበቱ የለሊቱ
ሲገለጥ እውነቱ ውበት አለው ለሊቱ
አቤት ውበቱ አቤት ውበቱ የለሊቱ
ሲታይ እውነቱ ውበት አለው ለሊቱ
የኑሮዬ ለሊት እንዲነጋ የማውቅበት
የሕይወቴ ለሊት ማዳኑን የማይበት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሊያባብለኝ በምድረበዳ ወሰደኝ
አስተምሮ አስተካክሎ ሊቀርፀኝ
በውዴ ላይ በርሱ ብቻ ተደግፌ
ይህች ማን ናት የሚሉኝን እንዳይ አልፌ
ያለኝን በሙሉ ወዲያ ማዶ
አሻገረው ብቻዬን ሊያይ ወዶ
ሲታገለኝ ቆየ በጨለማው
አስቸጋሪው ልቤን እስክረታው (፪x)
ሥሜን ሊቀይር አድኖም ሊያስቀረኝ
የሁለት ክፍል ሰራዊት ሊያረገኝ
ሥርዓቱን እማር ዘንድ አስጨነቀኝ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ