ሰው ክቡር ነው
Sew Kebur New
2005 · ትራክ 14 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ማንም ወንድሙን አይናቀው (፪x)
ያገኘም ያጣ ሰው ክቡር ነው (፪x)
ማንም ታናሹን አይናቀው (፪x)
ያገኘም ያጣ ሰው ክቡር ነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ለምን ተስፋ ይቁረጥ ለምንስ ይቆዝም
ዳቦ አይሁንበት አይራበው ፍቅር
ወንድሜ መገለሉ ይቅር (፫x)
ከእናቴም ባይወለድ
የአዳም ዘር የእግዜር ፍጡር
አብሬው ልቁረስ ልስጠው
እኔ በልቼ አይራበው
አያሳዝንም ወይ የራበው ሳያንሰው
አያሳዝንም ወይ ፍቅር ሲቸግረው
አያሳዝንም ወይ ጥግ ይዞ ሲያለቅስ
አያሳዝንም ወይ አንጀቱ ሲላወስ
መጽናናቱ (ልሁንለት )
እኔ እያለሁ (ወንድሜ አይሙት)
ትላንትና (እንዴት ይረሳል)
አፈር ባፈር (ላይ እንዴት ይኮራል)
አዝማች · Chorus
አያሳዝንም ወይ የራበው ሳያንሰው
አያሳዝንም ወይ ፍቅር ሲቸግረው
አያሳዝንም ወይ ጥግ ይዞ ሲያለቅስ
አያሳዝንም ወይ አንጀቱ ሲላወስ
መፅናናቱ (ልሁንለት)
እኔ እያለሁ (ወንድሜ አይሙት)
ትላንትና (እንዴት ይረሳል)
አፈር ባፈር (ላይ እንዴት ይኮራል)
ቁጥር 2 · Verse 2
ባልንጀራህን እንደራስህን ውደድ
ለራስህ የክብር ወንበር አትውሰድ
ጌታው ሲፈርድ ኋላ እንዳትወሰድ
ባልንጀራህን እንደራስህን ውደድ
ለራስህ ክብር ወንበር አትውሰድ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ