Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኦ ድንቅ ነህ

Oh Denq Neh

2005 · ትራክ 5 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ንፋሱ ሲታዘዝልህ ባሕሩም ሲታዘዝልህ

አየሁት ጌትነትህን ሁሉን ማድረግ መቻልህን (፪x)

ኦ ድንቅ ነህ ኦ (፪x)

ኦ ልዩ ነህ ኦ (፪x)

ልጠግብ አልቻልኩም አንተን አሞግሼ

ክበር እልሃለሁ መልሼ መላልሼ (፪x)

ኦ ድንቅ ነህ ኦ (፪x)

ኦ ልዩ ነህ ኦ (፪x)

እስከዛሬ በሕይወቴ እጅግ የተደነቅኩበት

አሰራር አደራረግህ እራሱም ያንተ ማንነት (፪x)

ኦ ድንቅ ነህ ኦ (፪x)

ኦ ልዩ ነህ ኦ (፪x)

ልጠግብ አልቻልኩምና አንተን አሞግሼ

ክበር እልሃለሁ መልሼ መላልሼ (፪x)

ኦ ድንቅ ነህ ኦ (፪x)

ኦ ልዩ ነህ ኦ (፪x)

ያደረክልኝ በዛ በዛ ከቁጥር በዛ

እንዲህ ነው ብዬ የምለውን ምላሽ እስካጣ (፪x)

ልጠግብ አልቻልኩምና አንተን አሞግሼ

ክበር እልሃለሁ መልሼ መልሼ (፪x)

ኦ ድንቅ ነህ ኦ (፪x)

ኦ ልዩ ነህ ኦ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ