ጌታን ማሰብ ነው
Gietan Maseb New
2005 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሆነው ነገር እርሱ የሚሆን ነው አሃ
የተደረገው እርሱ የሚደረግ ነው አሃ (፪x)
ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም
እግዚአብሔር ብቻ አይለመድም (፪x)
ሰው በእውቀቱ ላይ ደርቦ እውቀትን ቢጨምር
ይህም ከንቱ ነው ከንቱ
ለዓይኑ ያማረውን ከማድረግ ነፍሱን ባይከለክል
ይህም ከንቱ ነው ከንቱ
ማረፍያዬ ብሎ ቤቶቹን ቢያሳምር ቢያስጌጥ
ይህም ከንቱ ነው ከንቱ
ብርና ወርቅን አከማችቶ ለነገው ቢያስቀምጥ
ይህም ከንቱ ነው ከንቱ
አዝማች · Chorus
ለሰው ከድካሙ በቀር ትርፉ ምንድን ነው
ይልቅ በጉብዝናው ወራት ጌታን ማሰብ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሳይደክሙ ጌታን ማሰብ ነው
ሳይጨልም ጌታን ማሰብ ነው
በሩ ሳይዘጋ ጌታን ማሰብ ነው
ነፍስም ሳትወጣ ጌታን ማሰብ ነው
አይ ጐበዝ የተባለው ሰው አገር ሁሉ የሚያደንቀው
ጥሮ ግሮ ያከማቸውን ጥሎት ሄደ ሳይበላው ሃብቱን
ይሄም ከንቱ መድረሻው ምንድን ነው
እድሜውን ሁሉ ጠፍሮት ስንፍናው
እንደተባለ እንደቀረም መና እሱም ሄደ ሞት ቀደመውና
ሳይደክሙ ጌታን ማሰብ ነው
ሳይጨልም ጌታን ማሰብ ነው
በሩ ሳይዘጋ ጌታን ማሰብ ነው
ነፍስም ሳትወጣ ጌታን ማሰብ ነው
አዝማች · Chorus
ለሰው ከድካሙ በቀር ትርፉ ምንድን ነው
ይልቅ በጉብዝናው ወራት ጌታን ማሰብ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ