እግዚአብሔር አለ
Egziabhier Ale
2005 · ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የጭንቁ ጊዜ ሳይመጣ ግዳጅ ሳይሆንብኝ
አመልካለሁ በውዴታ አየተገዛሁ ለጌታ (፪x)
ግዴታዬን ለማክበር አይደለም የማመሰግነው
ይልቁንም ፍቅሩ ጨምሮብኝ አጣሁኝ የምለው (፪x)
ሳይወዱ ጌታ ነህ ቢሉት ቀን አስገድዷቸው
እኔ አስቲ ልዘምርለት ምቹ ሳለ ጊዜው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስንት የምለው ነገር በልቤ የለኝ
ቃላት አቅም አጣ ተቸገርኩ እያነሰብኝ
እኔ ከማቀርበው እልፍ የምስጋና ቃል
የእግዚአብሔር የአንድ ቀን ምሕረቱ ይመዝንብኛል
የሚያሳስበኝ እሱን አንዴት እንደማከብር ነው
የሚያሳስበኝ እሱን አንዴት እንደማስከብር ነው
የሚያሳስበኝ ጌታን አንዴት እንደማከብር ነው
የሚያሳስበኝ እሱን አንዴት እንደማስከብር ነው
አዝማች · Chorus
ነገር ጐደለ እግዚአብሔር አለ
ኑሮም ጐደለ እግዚአብሔር አለ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አንዳንድ ጊዜ አይደለም የማመሰግነው
ሲጐልም እሰየሁ ሲሞላም እሰየሁ
የማመሰግንበት ምክንያቴ የእግዚአብሔር ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ጌታ ካለ ቤቴ ሙሉ ነው (፪x)
እጠግባለሁ ፊቱን እያየሁ (፪x)
እሱ ካለ ቤቴ ሙሉ ነው (፪x)
እጠግባለሁ ፊቱን እያየሁ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
የሚያሳስበኝ አንተን አንዴት እንደማከብር ነው
የሚያሳስበኝ አንተን አንዴት እንደማስከብር ነው (፪x)
አፌን ሞልቼ እንድዘምረው
የሚጋብዘኝ ማንነትህ ነው (፪X)
ቁጥር 6 · Verse 6
ለማንነትህ ክብር ይድረስህ
ለማንነትህ ክብር ይሁንልህ
ለማንነትህ ክብር ይኸውልህ
ለማንነትህ ክብር ይሁንልህ
አዝማች · Chorus
ነገር ጐደለ እግዚአብሔር አለ
ኑሮም ጐደለ እግዚአብሔር አለ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ