የሚረባኝን የሚያውቅልኝ
Yemirebagnen Yemiyawqelegn
2005 · ትራክ 2 · 5:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሚረባኝን የሚያውቅልኝ (፪x)
ከአንተ በላይ ማንም የለኝ
እኔ ለራሴ ደካማ ነኝ
ከአንተ በላይ ማንም የለኝ
እኔ ለራሴ አቅምም የለኝ
አፈርኩበት : እኔ አውቃለው ባልኩበት
እኔ አውቃለው ባልኩበት
አፈርኩበት አስቢያለው ባልኩበት
አውቂያለው ባልኩበት
አዝማች · Chorus
አሁንማ ከአንተ ጋር ልስማማ (፪x)
እንግዲማ ከአንተ ጋር ልስማማ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ልጅ አባቱን ዳቦ ቢለው
ድንጋይ ወስዶ እንዳይሰጠው
ሰው መልካምን ማድረግ ካወቀ
የእግዚአብሔር ፍቅር ከሰው የላቅ (፪x)
አዝማች · Chorus
አሁንማ ከአንተ ጋር ልስማማ (፪x)
እንግዲማ ከአንተ ጋር ልስማማ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አፈርኩበት : እኔ አውቃለው ባልኩበት (፪x)
አፈርኩበት አስቢያለው ባልኩበት
አውቂያለው ባልኩበት
ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል
ነገም ስለ እራሱ ይጨነቃል
እግዚአብሔር ያለው ነው የሚሆነው
ዝም ብሎ የእርሱን ማዳን ማየት ነው
ቁጥር 4 · Verse 4
ነፍሴ አታውኪኝ አታስጨንቂኝ ፣ ተይ ተይኝ
እግዚአብሔር ያለው ይሁንልኝ ፣ ይሁንልኝ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ነፍሴ ልምከርሽ ቁም ነገር
እግዚአብሔር ስለሚወደው ነገር
ፍቃዴ ይሁን ብለሽ አትደምድሚ
ምን ይላል ጌታሽን ተስማሚ
ቁጥር 6 · Verse 6
ተይ ነፍሴ ተይ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ተይኝ (፫x)
ተይ ነፍሴ ተይ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ተይኝ
ተይ ኧረ ተይ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ተይኝ
ተይ ነፍሴ ተይ ተይኝ (በምህረቱ : ቸርነቱ : የሚከልልሽ)
አታስጨንቂኝ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ተይኝ (እንደ ንስር የሚያድስ ቃል ዋስ አለብሽ)
ተይ ነፍሴ ተይ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ተይኝ (ኧረ እግዚአብሔር ነዉ)
አታስጨንቂኝ ተይኝ (ታመኝዉ ፣ ታመኝዉ)
ተይ (ታመኝዉ) ነፍሴ ተይ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ተይኝ
ተይ (ታመኝዉ) ነፍሴ ተይ ተይኝ
አታስጨንቂኝ ተይኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ