Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አለኝ አባት

Alegn Abat

2005 · ትራክ 10 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሚያስፈልገኝን ያ'ረገልኝ ተንከባክቦ የሚያሳድገኝ

የሚሸከመኝ እንደልጅነቴ አለልኝ ቸሩ አባቴ (፪x)

አለኝ አባት አባት

የምመካበት አባት

አለኝ አባት አባት

'ማስፈራራበት አባት

ጠላቴ ሆይ ስማ ወዴት ወዴት

አትዘንጋው እንጂ አንዳለኝ አባት

እንደ ዓይኑ ብሌን 'ሚያስብ 'ሚጠነቀቅ

በልጁ የመጣበትን የማይምር የማይለቅ

አለኝ አባት አባት

የምመካበት አባት

አለኝ አባት አባት

ማስፈራራበት አባት

እግዚአብሔር አባቴ እኩያ የለውም

ግን እኮ ማንንም አይንቅም (፪x)

ይቅርታው ብዙ ሁልጊዜ የሚምር

መልካሙን መንገድ የሚያስተምር

ማማክረው የሚመክረኝ

አባቴ እያለ ምን አባዘነኝ

ሰውን ተስፋ ማድረጉ በቃኝ በቃኝ

ግራ ቀኝ ማየቱ በቃኝ በቃኝ

ጉዳይ አለኝ ከአንተ'ጋ መጥቻለሁ ላወጋ

ጉዳይ አለኝ ከአንተ'ጋ መጥቻለሁ ላወጋ

መጥቼም ሸክሜን አራግፋለሁ ጌታ

እንደማትሰለቸኝ ተማምኛለሁ ጌታ

ሁልጊዜ የፍቅር ብሩህ ፊት አለህ ጌታ

የሚያቀርብ የሚያስጠጋ ጌታ

ጉዳይ አለኝ ከአንተ'ጋ መጥቻለሁ ላወጋ

ጉዳይ አለኝ ከአንተ'ጋ መጥቻለሁ ላወጋ

ከአንተ ጋር ልቆራኝ ከአንተ ጋር ልወዳጅ

ይሄ ነው የሚረባ ይሄ ነው የሚበጅ (፬x)

ጉዳይ አለኝ ከአንተ'ጋ መጥቻለሁ ላወጋ

ጉዳይ አለኝ ከአንተ'ጋ መጥቻለሁ ላወጋ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ