Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ወደ ዕረፍቴ እገባለሁ

Wede Ereftie Egebalehu

2005 · ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በከንቱ እንዳለፋ ስለራራልኝ ስላዘነልኝ

የሕይወትን መንገድ አቅጣጫ አሳየኝ (፪x)

ያየሁትን መንገድ ይዤ እዘልቃለሁ (፪x)

እንደሄድኩም አልቀር ዕረፍቴ እገባለሁ እገባለሁ (፪x)

ወደ ዕረፍቴ እገባለሁ ወደ ዕረፍቴ

ወደ አገሬ እገባለሁ ወደ አገሬ (፪x)

ተስተጓጉዬ እንዳልቀር ሜዳ ላይ

የፊቴን ትቼ ግራና ቀኝ ሳይ

አሳይቶኛል አልፎበት መንገዱን

እከተላለሁ የርሱን ፍለጋውን

መንገዴ ነው የሱስ እውነት ሕይወት

ቀና ምሄድበት አብ ጋር ምደርስበት (፬x)

በከንቱ እንዳለፋ ስለራራልኝ ስላዘነልኝ

የሕይወትን መንገድ አቅጣጫ አሳየኝ (፪x)

ያየሁትን መንገድ ይዤ እዘልቃለሁ (፪x)

እንደሄድኩም አልቀር ዕረፍቴ እገባለሁ እገባለሁ (፪x)

ወደ ዕረፍቴ እገባለሁ ወደ ዕረፍቴ

ወደ አገሬ እገባለሁ ወደ አገሬ (፪x)

ሰፊው ጐዳና አማራጭ ስላለው

አልመኘውም ዳርቻው የሞት ነው

በጠባቡና በሕይወት መንገድ ላይ

እራመዳለሁ ተስፋይቷን እንዳይ

መንገዴ ነው የሱስ እውነት ሕይወት

ቀና ምሄድበት አብ ጋር ምደርስበት (፬x)

በከንቱ እንዳለፋ ስለራራልኝ ስላዘነልኝ

የሕይወትን መንገድ አቅጣጫ አሳየኝ (፪x)

ያየሁትን መንገድ ይዤ እዘልቃለሁ (፪x)

እንደሄድኩም አልቀር ዕረፍቴ እገባለሁ እገባለሁ (፪x)

ወደ ዕረፍቴ እገባለሁ ወደ ዕረፍቴ

ወደ አገሬ እገባለሁ ወደ አገሬ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ