ተሳልሜ አልሄድም
Tesalemie Alhiedem
2005 · ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አነጋልኝ ዛሬን በዕድሜዬ ጨመረው (፪x)
በስሙ ዋጅቼ ቀኑን ልጀምረው (፪x)
አይ አይ አይ አይ
ሳላመልክ በከንቱ አይ
አይለፍ ዕለቱ አይ አይ አይ
አምልኪው ተብዬ ተነግሮኝ ጀምሬ
አምልኩት እላለሁ እኔ ደግሞ ዛሬ
አምልኪው አምልኪው ተብዬ ጀምሬ
አምልኩት እላለሁ እኔ ደግሞ ዛሬ
እናም እግዚአብሔር የሚመለከው
ጠጋ ተብሎ ነው
እንዴ እግዚአብሐር የሚመለከው
በእውነት በመንፈስ ነው
አዝማች · Chorus
ማደሪያው ስር እሆናለሁ እንጂ
ዙፋኑ ስር እሰግዳለሁ እንጂ
ተሳልሜ አልሄድም ከደጅ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሃያራቱ ሽማግሌዎች ቅዱስ ቅዱስ
እልፍ አእላፍ መላእክቱ ቅዱስ ቅዱስ
ምስጋና አለው የተረፈ ከኔ የሚሻው ከቃሌ ባለፈ
አምልኮ አለው የተረፈ እኔም ልዘምር ከቃሌ ባለፈ
ሰው በከንፈሩ አምልኮ
ልቡን ከእግዚአብሔር ቢያርቀው
ልብን የሚመረምረው
የአፉን ቃል ብቻ አይሰማው (፪x)
አዝማች · Chorus
ማደሪያው ስር እሆናለሁ እንጂ
ዙፋኑ ስር እሰግዳለሁ እንጂ
ተሳልሜ አልሄድም ከደጅ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ለልቤ ጌታ ከልቤ
ለልቤ ንጉስ ከልቤ
እስኪ ልዘምር ከልቤ
ዛሬም እንደልጅነቴ (፪x)
እኔ ያመንኩትን አውቃለሁኝ ልንገረው የሚሻ
እኔ ያመንኩትን አውቃለሁኝ ልንገረው የሚሻ
ጌታ ነው የመጀመሪያ ጌታ ነው የመጨረሻ
አምላክ ነው የመጀመሪያ አምላክ ነው የመጨረሻ (፪x)
ሃይለኛ የመጀመሪያ ሃይለኛ የመጨረሻ
ታዋቂ የመጀመሪያ ታዋቂ የመጨረሻ
ዝነኛ የመጀመሪያ ዝነኛ ነው የመጨረሻ
ንጉስ ነው የመጀመሪያ ንጉስ ነው የመጨረሻ
ጌታ ነው የመጀመሪያ ጌታ ነው የመጨረሻ
አምላክ ነው የመጀመሪያ አምላክ ነው የመጨረሻ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ