አይናፍቀኝም አገሩ
Aynafqegnem Ageru
2005 · ትራክ 7 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አይናፍቀኝም ሃገሩ ያ ጨለማ ያ ሃሩሩ
ነፃ አውጥቶኛል ጌታዬ በነፃነት ልኖር እፎይ ብዬ (፪x)
አራገፈና ሸክሜን ያጎበጠኝን ቀንበሬን
አሸክሞኛል የራሱን የቀለለ የለዘበውን
አሸክሞኛል ፍቅሩን እየገለፀ ትርጉሙን
አሸክሞኛል ፀጋውን እንድመሰክር ስራውን
አዝማች · Chorus
እገዛለታለሁ በደስታ አሸንፎኛል ይሄ ጌታ
በሰው ፍቅር የወደቀ እንኳን ይሰጥ የለ ወይ እራሱን
ኧኸይ በፍቅሩ ገመድ ኧኸይ ተጠፍሬያለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
ኧኸይ ውሎ እያደረ አያይ አያይ ልቤን እረታው
ሁለት ጌቶች አይገዙኝም ጉዳዬ ሌላ አልደብልም
እግዚአብሔር ስላለው ብልጫ አያዳግትም ለምርጫ
እግዚአብሔር ስላለው ብልጫ አያስቸግርም ለምርጫ
እግዚአብሔር ስላለው ብልጫ አያዳግትም ለምርጫ
አዝማች · Chorus
እገዛለታለሁ በደስታ አሸንፎኛል ይሄ ጌታ
በሰው ፍቅር የወደቀ እንኳን ይሰጥ የለ ወይ እራሱን
ኧኸይ በፍቅሩ ገመድ ኧኸይ ተጠፍሬያለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
ኧኸይ ውሎ እያደረ አያያዬዬ ልቤን እረታው
ዝም ብዬ እንዴት እኖራለሁ
ላገኘሁት እጄን እያነሳሁ
አልሟገትም እያልኩ ምን አለበት
የእግዚአብሔር ፍቃድ ያልሆነ እሱ ሞት አለበት
አልቀጥፈውም እጄን ሰድጄ ዛሬ
የሚያጠፋ የሚገ'ለውን የሞት ፍሬ
ይቅርብኝ እንጂ ከንቱ ከንቱ ጨዋታ
አሳስቆ ይለይ የለ ወይ ከውዱ ጌታ (፪x)
ዝም ብዬ እንዴት እኖራለሁ
ላገኘሁት እጄን እያነሳሁ
አልሟገትም እያልኩ ምን አለበት
የእግዚአብሔር ፍቃድ ያልሆነ እሱ ሞት አለበት
አልቀጥፈውም እጄን ሰድጄ ዛሬ
የሚያጠፋ የሚገ'ለውን የሞት ፍሬ
ይቅርብኝ እንጂ ከንቱ ከንቱ ጨዋታ
አሳስቆ ይለይ የለ ወይ ከውዱ ጌታ (፪x)
<poem>
አይናፍቀኝም ሃገሩ ያ ጨለማ ያ ሃሩሩ
ነፃ አውጥቶኛል ጌታዬ በነፃነት ልኖር እፎይ ብዬ (፪x)
አይናፍቀኝም ሃገሩ ያ ጨለማ ያ ሃሩሩ
ነፃ አውጥቶኛል ጌታዬ በነፃነት ልኖር እፎይ ብዬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ