Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አቤቱ በአንተ ታምኛለሁ

Abietu Beante Tamegnalehu

2006 · ትራክ 5 · 7:55 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አቤቱ በአንተ ታምኛለሁኝ (፪x)

ኢየሱስ በአንተ ታምኛለሁኝ (፪x)

አንተ አምላኬ ነህ ለዘለዓለም

አንተ ንጉሤ ነህ ለዘለዓለም

መታመኛዬ ነህ ለዘለዓለም ፣ ለዘለዓለም (፪x)

ከአንተ በቀር በጐነት የለኝም ጌታ

ከአንተ በቀር በጐነት የለኝም

ከአንተ በቀር በጐነት የለኝም ኢየሱስ

ከአንተ በቀር በጐነት የለኝም (፪x)

የተማመንኩብህ የነፍሴ አለኝታዬ

ለሕይወቴም ዋስትና ሆነሃል ጌታዬ (፪x)

መንፈሴን በሐሴት በደስታ ሞልተህ

ያለ አንዳች ሥጋት ታኖረኛለህ ፣ ታኖረኛለህ

ዕድል ፈንታዬ ነህ ጌታ

ዕድል ፈንታዬ ነህ

ዕድል ፈንታዬ ነህ ኢየሱስ

ዕድል ፈንታዬ ነህ (፪x)

የውስጥ የልቤን በር በፍቅር አንኳኩተህ

ክፈትልኝ ብለህ ፈቃዴን ጠይቀህ ወደ ልቤ ገብተህ

ድካምሽን ስጭኝ እኔ ልሸከመው

የሚል የልብ ወዳጅ ጌታ አንተን ብቻ አየሁ (፪x)

ዕድል ፈንታዬ ነህ ጌታ

ዕድል ፈንታዬ ነህ

ዕድል ፈንታዬ ነህ ኢየሱስ

ዕድል ፈንታዬ ነህ (፪x)

አቤቱ በአንተ ታምኛለሁኝ (፪x)

ኢየሱስ በአንተ ታምኛለሁኝ (፪x)

አንተ አምላኬ ነህ ለዘለዓለም

አንተ ንጉሤ ነህ ለዘለዓለም

መታመኛዬ ነህ ለዘለዓለም ፣ ለዘለዓለም (፪x)

ከአንተ በቀር በጐነት የለኝም ጌታ

ከአንተ በቀር በጐነት የለኝም

ከአንተ በቀር በጐነት የለኝም ኢየሱስ

ከአንተ በቀር በጐነት የለኝም (፪x)

መሸከም ቢያቅተኝ የሸክሙን ክብደት

በፊትህ አስቀመጥኩት የጉድለቴን ብዛት (፪x)

እርዳታህ ከሠማይ ሲመጣልኝ ድንገት

የከበደኝ ሁሉ ተንሳፎ አየሁት (፪x)

ዕድል ፈንታዬ ነህ ጌታ

ዕድል ፈንታዬ ነህ

ዕድል ፈንታዬ ነህ ኢየሱስ

ዕድል ፈንታዬ ነህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ