ገረመኝ
Geremegn
2006 · ትራክ 2 · 6:48 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የትኛው ወዳጅ ነው የትኛው አባት
እስከ ዛሬ ድረስ ሳይደክም ሳይታክት
ሊሸከም የሚወድ ከኃጥያት ከነክፋቴ
ጌታ አንተን ብቻ አየሁ ፍፁም አፍቃሪዬ
አዝማች · Chorus
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ይገርማል መወደዴ ይገርማል መፈለጌ
ይገርማል መመረጤ ይገርማል መፈጠሬ
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ንጉሥ አዋጅ ቢያውጅ ጠላቴ ተጣድፎ
እርግማን ሊረግመኝ ባላቅም ተቻኩሎ
በለአም ግን ትእዛዝ ከላይ ተቀበለ
አዋጅ ሻረ ጌታ ታሪክ ተለወጠ
አዝማች · Chorus
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ (፪x)
ይገርማል መታሰቤ በዓይኖቹ መታየቴ
ገረመኝ እኔ መትረፌ በእጆቹ መያዜ
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፫x)
ቁጥር 5 · Verse 5
የመኖሬን ሚስጢር ሳስብ ይደንቀኛል
ዛሬ ላይ መቆሜ እጅግ ይገርመኛል
አንተ ከላይ ሆነህ በዓይኖችህ አየኸኝ
ምህረት ማፅናናትህ እጅግ ደስ አሰኘኝ
አዝማች · Chorus
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ (፪x)
ይገርማል መወደዴ ይገርማል መፈለጌ
ይገርማል መፈቀሬ ይገርማል መመረጤ
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ
ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ ፣ ደነቀኝ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ማንም ያልራራልኝ መንገድ የተጣልኩኝ
በደም ተነክሬ ሞቴን የጠበቅሁኝ
በእጅህ ታክሜ ድኜ ከህመሜ
ከመሞት አምልጬ ገረመኝ መቆሜ
አዝማች · Chorus
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፬x)
ቁጥር 8 · Verse 8
ይገርማል ኧረ መትረፌ ከክፉዎች ማምለጤ
ገረመኝ አሰራርህ ፍጥነትህ አደራረስህ
ገረመኝ ፣ ገረመኝ ፣ ገረመኝ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ