ከፍ በል
Kef Bel
2006 · ትራክ 11 · 6:02 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ከፍ በል (፬x)
በምሥጋና ከፍ በል በዝማሬ ከፍ በል
በምሥጋና ከፍ በል በዝማሬ ከፍ በል
ከፍ ካለው በላይ ከፍ ላልከው
ለአንተ ምሥጋናን እሰጣለሁ (፪x)
ሥምህን ጠርቼ አላፈርኩምና
ድንቅህ ለሕይወቴ ብዙ ነውና
ፊትህ ወድቄ ላቅርብ ምሥጋናዬን
ከፍ ከፍ ላርግህ ባለውለታዬ
ከፍ በል (፬x)
በምሥጋና ከፍ በል በዝማሬ ከፍ በል
በምሥጋና ከፍ በል በዝማሬ ከፍ በል
ከፍ ካለው በላይ ከፍ ላልከው
ለአንተ ምሥጋናን እሰጣለሁ (፪x)
ጠላት ሊይዘኝ ከኋላዬ መጥቶ
ባህሩም ሲናወጥ እስከ አፉ ሞልቶ
በዘረጋሁ ጊዜ በትሬን በእምነት
በድል ተሻገርኩ ሰጠመ ጠላት
አምላኬ ነህ አምላኬ (፮x)
አይቻለሁ ማዳንህን
አይቻለሁ ጥበቃህን
አይቻለሁ ችሎታህን
አይቻለሁ ብርታትህን
አይቻለሁ ምህረትህን
አይቻለሁ ያን ፍቅርህን
አይቻለሁ ጉልበትህን
አይቻለሁ ስልጣንህን
እንደ እግዚአብሔር ያለ ኧረ ማን አለ (፪x)
እንደ ኢየሱስ ያለ እስኪ ማን አየ (፪x)
ይናገር ማን አየ ኧረ ማን አየ
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
እንደ ኢየሱስ ያለ ማንም የለም (፪x)
አንተን ማን ይመስላል በዘመናት መሃል
ከአንተስ ጋር እግዚአብሔር ማን ይወዳደራል
የነገሥታት ንጉሥ የኃይላን ኃያል
ገናናው እግዚአብሔር አንተን ማን ይመስላል
እንደ አንተ ያለ የለም (፪x)
እንደ አንተ ያለ የለም ለዘለዓለም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ