ምን ይሳንሃል
Men Yesanehal
2006 · ትራክ 3 · 6:21 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል
ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል
ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል
ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል
ጌታ ሆይ ለአንተ ምን ይሳንሃል
ኢየሱስ ሆይ ለአንተ ምን ያቅትሃል (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የእስራኤልን ሕዝብ ከባርነት ምድር
በውኑ ሊያወጣ ሙሴ ማን ነበር
አፌን በአፍህ ላይ አደርጋለሁ ብለህ
ላክኸው ወደ ፈርዖን ኮልታፋውን መርጠህ
በችሎታህ ታምነህ ይህን ትሰራለህ
ይህን ታደርጋለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል
ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል
ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል
ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል
ጌታ ሆይ ለአንተ ምን ይሳንሃል
ኢየሱስ ሆይ ለአንተ ምን ያቅትሃል (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ብዙ የተማሩ አዋቂዎችን ትተህ
ዓሣ አጥማጆችን ለራስህ መረጥህ
እጅግ ታናናሾች ተራ በተባሉት
ዓለምን አዳረስክ በወንጌልህ እሳት
በችሎታህ ታምነህ ይህን ትሰራለህ
ይህን ታደርጋለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል
ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል
ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል
ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል
ጌታ ሆይ ለአንተ ምን ይሳንሃል
ኢየሱስ ሆይ ለአንተ ምን ያቅትሃል (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ልባቸው ሲቀልጥ በዮርዳኖስ ሙላት
ታቦት ተሸክሙ እነዚያ ካህናት
በተንጣለለው ወንዝ ሰገባ እግራቸው
ለሁለት ከፍለህ አንተ አሻገርካቸው
በችሎታህ ታምነህ ይህን ትሰራለህ
ይህን ታደርጋለህ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል
ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል
ምን ይሳንሃል ምን ያቅትሃል
ሁሉ ይቻልሃል ሁሉ ይቻልሃል
ጌታ ሆይ ለአንተ ምን ይሳንሃል
ኢየሱስ ሆይ ለአንተ ምን ያቅትሃል (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ለመሞት ጥቂት ቀን የቀራትን አይተህ
እንድትመግበው ደሃዪቱን አዘህ
ከኮራት ፈፋ ውስጥ ጌታ አውጥተኸው
በሰራፍታ ምድር ኤሊያስን መገብኸው
በችሎታህ ታምነህ ይህን ትሰራለህ
ይህን ታደርጋለህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ