አንተው ትሻለኛለህ
Antew Teshalegnaleh
2006 · ትራክ 10 · 8:01 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የንጉሥ ልጅነት እንቢ ያለ
ግብፅንም በእምነት የተወ
ሳያየው እንደሚያየው ቆጥሮ
ብድራቱን አይቶ አሻግሮ
ምንም እንኳን የግብፅን ጥበብን ቢማርም
ሙሴ የባእድ ዕውቀት ከቶ አልማረከውም
ከገንዘብም ይልቅ መከራን መረጠ
ስለ ሥምህ ለአንተ መነቀፍን ወደደ
አዝማች · Chorus
ለጊዜያዊ እርካታና ደስታ
አለውጥም የነፍሴን ጌታ
ብድራቴን ልየው አሻግሬ
የዓለምን ዝናን ክብሯን ሁሉ ንቄ
አንተ ትሻለኛለህ (፰x)
አንተ ታዋጣኛለህ (፰x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በቁጥቋጦው መሃል ታየኸው
እግዚአብሔር አምላኩ ቀረብከው
ሾምክና ወደ ሕዝብህ ላክኸው
በሞገስ ወጣህና አብረኸው
በብርታትህ ጉልበት የበረታ ሆነ
በድፍረት ንጉሥ ፊት ለመቆም ታመነ
የሰጠኸውን በትር በእምነት ይዞ ወጣ
እስራኤልን ከግብፅ ባርነት አወጣ
አዝማች · Chorus
ለጊዜያዊ እርካታና ደስታ
አለውጥም የነፍሴን ጌታ
ብድራቴን ልየው አሻግሬ
የዓለምን ዝናን ክብሯን ሁሉ ንቄ
አንተ ትሻለኛለህ (፰x)
አንተ ታዋጣኛለህ (፰x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ትሁት ሆኖ ተመላለሰ
በህዝቡ መቃወም ታገሰ
እንዳለው ወደ አንተ ማለደ
ጥፋቱን ማየት መች ወደደ
ብድራቱን አይቶ ለዓላማው ጨክኖ
የንጉሥ ልጅ ሲባል በእምነት እንቢ ብሎ
ሳይፈራና ሳይደነግጥ የንጉሡን ቁጣ
በትሩን አነሳ ጠላትን ድል ነሳ
አዝማች · Chorus
ለጊዜያዊ እርካታና ደስታ
አለውጥም የነፍሴን ጌታ
ብድራቴን ልየው አሻግሬ
የዓለምን ዝናን ክብሯን ሁሉ ንቄ
አንተ ትሻለኛለህ (፰x)
አንተ ታዋጣኛለህ (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ