አምላኬ
Amlakie
2006 · ትራክ 9 · 7:00 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አምላኬ ከአማልክት በላይ
ታላቅ ነውና ሃሃ (፫x)
ጌታዬ ከአማልክት በላይ
ታላቅ ነውና ሃሃ (፫x)
በፊቱ እጣንን ከማጠን በቀር
አምልኮ ስግደትን ከማቅረብ በቀር
ምሥጋናን ዝማሬን ከመስጠት በቀር
ያለኝን በፊቱ ከማፍሰስ በቀር
ሌላ ምን እሰጥሃለሁ ሌላ (፬x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሠማይ ከሠማያት በላይ
ከፍ ብሎ ቢኖር ሌላ ሠማይ
ጌታዬን ሊይዘው አይችልም
ነውና ከሁሉም የበላይ (፪x)
የለውም የበላይ የበላይ የለውም የበላይ
እርሱ ነው የበላይ የበላይ እርሱ ነው የበላይ
ጌታዬ ነው የበላይ የበላይ ጌታ ነው የበላይ
አዝማች · Chorus
አምላኬ ከአማልክት በላይ
ታላቅ ነውና ሃሃ (፫x)
ጌታዬ ከአማልክት በላይ
ታላቅ ነውና ሃሃ (፫x)
በፊቱ እጣንን ከማጠን በቀር
አምልኮ ስግደትን ከማቅረብ በቀር
ምሥጋናን ዝማሬን ከመስጠት በቀር
ያለኝን በፊቱ ከማፍሰስ በቀር
ሌላ ምን እሰጥሃለሁ ሌላ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አየሁኝ የእርሱን ታላቅነት
ተረዳሁ የብርታቱን ጉልበት
ፅኑ ነው የለም ከእርሱ በቀር
በሠማይ ቢሆን በዚህች ምድር (፪x)
እርሱ ነው የበላይ የበላይ እርሱ ነው የበላይ (፪x)
ጌታዬ ነው የበላይ የበላይ ጌታ ነው የበላይ
አዝማች · Chorus
አምላኬ ከአማልክት በላይ
ታላቅ ነውና ሃሃ (፫x)
ጌታዬ ከአማልክት በላይ
ታላቅ ነውና ሃሃ (፫x)
በፊቱ እጣንን ከማጠን በቀር
አምልኮ ስግደትን ከማቅረብ በቀር
ምሥጋናን ዝማሬን ከመስጠት በቀር
ያለኝን በፊቱ ከማፍሰስ በቀር
ሌላ ምን እሰጥሃለሁ ሌላ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በብርቱ ጉልበቱ ታመንኩኝ
በፅድቅም ስራው ተመካሁኝ
በክንዱ ሁሉንም ያዘዘ
የምድርን ዳርቻ የያዘ
ላድንቀው ዛሬም የእኔን ጌታ
ላክብረው በጣፋጩ ዜማ
ገዥ ነህ ሁሉንም የረታህ
እያልኩኝ የለህም የበላይ
የለህም የበላይ የበላይ የለህም የበላይ (፪x)
አንተ ነህ የበላይ የበላይ አንተ ነህ የበላይ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ