ነፍሱን
Nefsun
2006 · ትራክ 7 · 6:38 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ነፍሱን እስከ መስጠት ወደደኝ
የፍቅሩ ምርኮኛ አደረገኝ
ሳይዋጋ እኔን ማረከኝ
ሳይታገል ፍቅሩ አሸነፈኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔም በተራዬ እንዳቅሜ
ምላሼ ይሄ ነው ወዳጄ
ደስ ካለህ ውዴ መውደዴ
ይኸው እገልፃለሁ ማፍቀሬን
ያለኝን ክብሬን እጥላለሁ
ከእግርህ ሥር ወድቄ እሰግዳለሁ
የነፍሴ ወዳጅ ነህ ኢየሱሴ
በፊትህ ልስበረው ጠርሙሴን
ከእግርህ ስር ይፍሰስ ሽቶዬ
ፍቅሬን መግለጫ ነው ጌታዬ (፪x)
መውደዴን እገልፃለሁ መውደዴን (፬x)
እወድሃለሁ (፰x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አጥፊዬ ተነስቶ ሊያጠፋኝ
የሞት ጣር ይዞ ሲያስፈራራኝ
ጠላቴም ሞትን ሲመኝልኝ
አንተ ነህ ሕይወት ያወጅክልኝ
አጥፊዬ ተነስቶ ሊያጠፋኝ
የሞት ጣር ይዞ ሲያስፈራራኝ
ጠላቴም ሞትን ሲመኝልኝ
አንተ ግን በቅን ፈረድክልኝ
አዝማች · Chorus
እኔም በተራዬ እንዳቅሜ
ምላሼ ይሄ ነው ወዳጄ
ደስ ካለህ ውዴ መውደዴ
ይኸው እገልፃለሁ ማፍቀሬን
ያለኝን ክብሬን እጥላለሁ
ከእግርህ ሥር ወድቄ እሰግዳለሁ
የነፍሴ ወዳጅ ነህ ኢየሱሴ
በፊትህ ልስበረው ጠርሙሴን
ከእግርህ ስር ይፍሰስ ሽቶዬ
ፍቅሬን መግለጫ ነው ጌታዬ (፪x)
መውደዴን እገልፃለሁ መውደዴን (፬x)
እወድሃለሁ (፰x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ለዘለዓለም ለአንተ ታጨኹኝ
በፍቅሩ ጥልቀት ተወደድኩኝ
ንጉሤን ውበቴን ወደሃል
ላትተወኝ ቃል ገብተህልኛል (፪x)
እወድሃለሁ (፰x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ