Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኃይልን የሚያስታጥቀኝ

Hailen Yemiyastateqegn

2006 · ትራክ 4 · 6:58 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ኃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴን የሚያቀና

እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች የሚያበረታ

በኮረብቶች ላይ ሊያቆመኝ የወደደዉ

ለእጆቼ ሰልፍን ዘመቻን ያስተማረዉ (፪x)

ብርቱ አድርጐ ያቆመኝ ብርቱ አድርጐ (፬x)

ይሄ ነው እግዚአብሔር እርሱ ይሄ ነዉ

ይሄ ነው አምላኬ እርሱ ይሄ ነዉ

ይሄ ነው እግዚአብሔር እርሱ ይሄ ነዉ

ብርቱ አድርጐ የሚያቆም ብርቱ አድርጐ (፬x)

አስጨናቂዎቼ የለጠጡብኝ ቀስት ከቶ አልደረሰብኝ (፪x)

ብርቱ ተዋጊ ነው አምላኬ እግዚአብሔር በዓይኑ ሰበረልኝ (፪x)

ከመቅደሱ ጢስ ወጥቶ ጠላቴን በተነ

የማይወድቅ የመሰለውን ብርቱውን ዘረረ (፪x)

ኃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴን የሚያቀና

እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች የሚያበረታ

በኮረብቶች ላይ ሊያቆመኝ የወደደዉ

ለእጆቼ ሰልፍን ዘመቻን ያስተማረዉ (፪x)

ብርቱ አድርጐ ያቆመኝ ብርቱ አድርጐ (፬x)

እጁ ተዘርግቷል ማንም አይመልስም (፫x)

እርሱን የሚነካ ማን አለ የሚደፍረው (፫x)

የየቀኖቹ ክፋት እኔን እንደሚያገኘኝ

በክንፎቹ ጋርዶ በቀኙ ሰወረኝ (፪x)

ኃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴን የሚያቀና

እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች የሚያበረታ

በኮረብቶች ላይ ሊያቆመኝ የወደደዉ

ለእጆቼ ሰልፍን ዘመቻን ያስተማረዉ (፪x)

ብርቱ አድርጐ ያቆመኝ ብርቱ አድርጐ (፬x)

ተስፋ ያደረግሁት አምላኬ ብርቱ ነው

ብርቱ አድርጐ አቆመኝ ፣ ብርቱ አድርጐ አቆመኝ

ለእጆቼ ሰልፍን ለጠላቴም ዘመቻን

ውጊያን አስተማረኝ ፣ ውጊያን አስተማረኝ

በጠላቴ ፊት ለፊት በዘይቱ ቀባኝ

ሙ ሉ ኃይልን አስታጥቆ በክብር አቆመኝ (፪x)

ኃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴን የሚያቀና

እግሮቼን እንደ ብሆር እግሮች የሚያበረታ

በኮረብቶች ላይ ሊያቆመኝ የወደደዉ

ለእጆቼ ሰልፍን ዘመቻን ያስተማረዉ (፪x)

ብርቱ አድርጐ ያቆመኝ ብርቱ አድርጐ (፬x)

ይሄ ነው እግዚአብሔር እርሱ ይሄ ነዉ

ይሄ ነው አምላኬ እርሱ ይሄ ነዉ

ይሄ ነው እግዚአብሔር እርሱ ይሄ ነዉ

ብርቱ አድርጐ የሚያቆም ብርቱ አድርጐ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ