ክበር አንተ ብቻ
Keber Ante Becha
2006 · ትራክ 1 · 4:54 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እነዚያስ ያንን የተማመኑበት
ተሰነካከለ ተስፋ ያደረጉበት
ክብራቸው ወደቀ ቀንዳቸው ተመታ
በዙፋኑ ከብሮ አለ የእኛ ጌታ
ብቻህን ተዐምራት ያደረግህ ጌታ
ፍፁም የማትረታ
አዝማች · Chorus
በሠማይ በምድር ከቶ የለህ አቻ
ክበር አንተ ብቻ ንገሥ አንተ ብቻ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሠማይን እንደ መጋረጃ ዘርግቶ
እልፍኙን በውኃ አሳምሮ ሰርቶ
ምንም የሌለበት እጅግ ከደረቀ
አለቱን ሰንጥቆ ውሃን አፈለቀ (፪x)
አዝማች · Chorus
በሠማይ በምድር ከቶ የለህ አቻ
ክበር አንተ ብቻ ንገሥ አንተ ብቻ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሸለቆን የሚሞላ ተራራን የሚንድ
አገልጋዩን እንደ ነበልባል የሚያነድ
በተራሮች ላይ ውሆችን የሚያቆም
እንደ እግዚአብሔር ያለ ታላቅ አምላክ የለም
አዝማች · Chorus
በሠማይ በምድር ከቶ የለህ አቻ
ክበር አንተ ብቻ ንገሥ አንተ ብቻ
ቁጥር 4 · Verse 4
በሚንበለበለው እሳት ውስጥ ቢከተን
የምታምኑት አምላክ ያድናችሁ ቢለን
የምናምነው አምላክ ዝም ብሎ አያየን
ነጥቆ ያወጣናል ከእሳቱ ወላፈን (፪x)
አዝማች · Chorus
በሠማይ በምድር ከቶ የለህ አቻ
ክበር አንተ ብቻ ንገሥ አንተ ብቻ
ቁጥር 5 · Verse 5
መዝገቡም ይከፈት ታሪክም ይመርመር
አንደበትም ያውራ መስካሪም ይመስክር
ብርቱ የሆነ አምላክ ማነው ከአንተ በቀር
የሚነደውን እሳት በእሳት የሚሽር (፪x)
አዝማች · Chorus
በሠማይ በምድር ከቶ የለህ አቻ
ክበር አንተ ብቻ ንገሥ አንተ ብቻ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ