Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተወዳዳሪ የለህም

Tewedadari Yelehem

2006 · ትራክ 8 · 5:02 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አቻና ተወዳዳሪ የለህም

ብቻህን ኢየሱስ ጌታ ነህ (፫x)

እንዴት እንዳቆምካት ምድርና መሰረቷን

በምን እንዳፀናሃት የድንጋይ ማእዘኗን

ብቻህን ጌታ ነህ (፬x)

የባሕር ዳር ድንበሩን ለአንተ ማን አሳየህ

ሁሉ በቃልህ ሆነ ሰምቶህ እየታዘዘህ (፪x)

አቻና ተወዳዳሪ የለህም

ብቻህን ኢየሱስ ጌታ ነህ (፫x)

ከአህዛብ ጥበበኞች የሚመስልህ ማን አለ

ከመንግሥታቸውም ውስጥ ተወዳዳሪ የለህ

ብቻህን ጌታ ነህ (፬x)

ሁሉም ፍጥረት በፊትህ ለአንተ ይንበረከካሉ

ወደዱም ጠሉም ለክብርህ ወድቀው ይሰግዳሉ (፪x)

አቻና ተወዳዳሪ የለህም

ብቻህን ኢየሱስ ጌታ ነህ (፫x)

ይሄ የሰማነው ምንኛ እጅግ ጥቂት ነው

የኃይሉንስ ነጐድጓድ የሚያስተውለው ማነው

ብቻውን ጌታ እኮ ነው (፬x)

ትልቅ ነው እርሱ እግዚአብሔር ሃሳቡን የሚያውቅ ማነው

በሠማይም በምድር እኩያ አቻ የሌለው (፪x)

አቻና ተወዳዳሪ የለህም

ብቻህን ኢየሱስ ጌታ ነህ (፫x)

ብቻህን ጌታ ነህ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ