Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተመስገን

Temesgen

2006 · ትራክ 6 · 5:23 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ተመሥገን (፲x)

ከአብ ዘንድ ያለኸኝ ለእኔ ጠበቃዬ

በፍቅር የምታየኝ ወዳጅ አፍቃሪዬ

ፈልጌ የማላጣህ የምትቆም ከጐኔ

አንተ ነህ ኢየሱስ ድጋፍ መከታዬ (፪x)

ልዩ ወዳጄ ነህ ቋሚ ተጠሪዬ

ለሚደርስብኝም ነህ ተቆርቋሪዬ

ከእኔ የማትለይ የማትጠፋ ከጐኔ

አንተ ነህ ኢየሱስ ተሟጋች ለነፍሴ (፪x)

ተመሥገን (፲x)

ከገመትኩት በላይ ፍቅሩ ለእኔ በዛ

ፍፁም አይገመት እንዲህ እንደ ዋዛ

ግርዶሼን ቀደደው ልጁን አድርጐ ቤዛ

እግዚአብሔር ወደደኝ በፍቅሩ እኔን ገዛ (፪x)

ፍቅሩ እጅግ ግሩም ነው ከሁሉም የሚስብ

ያየ የሰማውን እጅግ የሚያስደንቅ

በከበረው ዙፋን ነፍሴን አኖረልኝ

ሁሉንም ድል አድርጐ ድል አወጀልኝ (፪x)

ተመሥገን (፲x)

መላእክት ተደፍተው ለሚሰግዱልህ

ቅዱስ ቅዱስ ብለው ለሚያዜሙልህ

እኔም ተነስቼ ቅዱስ ነህ እላለሁ

ከእግርህ ሥር ወድቄ ክብርን እሰጣለሁ (፪x)

በዕልልታ ሽብሸባ ቤትህ እገባለሁ

ሁሌም አምላኬ ነህ እገዛልሃለሁ

ለአንተ የሚሳንህ አላየሁምና

ዛሬም እልሃለሁ ይብዛልህ ምሥጋና

ዛሬም ነገም ለአንተ ይብዛልህ ምሥጋና (፪x)

ተመሥገን (፲x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ