Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዙሪያየ ሲጨልምብኝ

Abietu Endante manew

ትራክ 3 · 6:16 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

https://www.youtube.com/watch?v=18KJy0-ell8

ዙሪያየ ሲጨልምብኝ መሄጃ ግራ ሲገባኝ

ዓይኖቼን ወደአንተ አቀናሁ አባባ ፍጠንልኝ አልሁኝ

አንተም አንጐዳጐድክና ጠላቴንም በተንክና

ዳግም አጽንተህ አቆምከኝ ብርቱ ጦርኛም አረከኝ

በሀዝን ችግሬ ጊዜ አይዞህ ባይ ደራስሽ አጋዤ

ስጠራህ ፈጥነህ የምትደርስ ሳነባ እንባዬን ምታብስ

አቤቱ እንዳንተ ማነው አባባ (ኢየሱስዬ) እንዳንተ ማነው(፪x)

ጠላቴ ወጥመድ ዝርግቶ በብርቱ ነፍሴን ፈልጐ

ዙሪያዬን ሲዞር ሲያደባ ሲዶልት ከጁ ሊያስገባ

አንተ ግን ጌታ እግዚአብሔር ጻድቅ ነህ በቅን የምትፈርድ

ወጥመዱን ሰባበርክልኝ ከለላ አንባዬ ሆንክልኝ

በሀዝን ችግሬ ጊዜ አይዞህ ባይ ደራስሽ አጋዤ

ስጠራህ ፈጥነህ የምትደርስ ሳነባ እንባዬን ምታብስ

አቤቱ እንዳንተ ማነው አባባ (ኢየሱስዬ) እንዳንተ ማነው(፪x)

በምክርህ አንተ ግሩም ነህ ሁሉን በፍቅር የያዝህ

ምሬቴን ከእኔ አውጥተሃል በፍቅር ቃል አጽናንተኸኛል

የሚጤስ ጧፌን ያበራህ ቅጥቅጥ ሸንበቆዬን ያጸናህ

እንዳንተ ማን አለ ጌታ ምን ልክፈል ለአንተስ ውለታ

በሀዝን ችግሬ ጊዜ አይዞህ ባይ ደራስሽ አጋዤ

ስጠራህ ፈጥነህ የምትደርስ ሳነባ እንባዬን ምታብስ

አቤቱ እንዳንተ ማነው አባባ (ኢየሱስዬ) እንዳንተ ማነው(፪x)

እንዳንተ ማንው ማ ነው?

እንዳንተ ማነው አባባ ኢየሱስ(ለእኔ የደረሰ)(፪x)

አንተን ብዬ ስምህን ጠርቼ

መች አፍሬ አውቃለሁ ጌታ

አመልክሃለሁ ጥዋት ማታ

[አመልክሃለሁ(፫x)](፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ