ጌታ እኮ ነህ
Gieta Eko Neh
ትራክ 12 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ካለመኖር ወደመኖር ታመጣለህ
ቃል ይውጣ እንጂ ምንተስኖህ ትሰራለህ
ኢየሱስ ጌታ ነህ (፪x)
አባቴ ጌታ ነህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በሞተው ነገር ላይ ነፍስ ህይወትን ዘርተህ (ጌታ እኮ ነህ (፪x))
ታኖራለህ ጌታ መቃብርን ከፍተህ (ጌታ እኮ ነህ (፪x))
አዋጅን በአዋጅ ስትሽር አይቻለሁ (ጌታ እኮ ነህ (፪x))
ታሪክ ተገልብጦ እንዲህ እዘምራለሁ (ጌታ እኮ ነህ (፪x))
ጨለማ በፊቴ አይጨልምም
ጌታ ነህ ኢየሱስ ለዘለዓለም
እኔማ ኧረ እንዴት ዝም እላለሁ
ከሞት ያመለጥኩት በአንተ እኮ ነው
ጌታ የእኔ ማረፊያ ጌታ መታመኛዬ አዎ
ጌታ ስንቱን አለፍኩት ጌታ በአንተ ትምኜው
አዝማች · Chorus
ካለመኖር ወደመኖር ታመጣለህ
ቃል ይውጣ እንጂ ምንተስኖህ ትሰራለህ
ኢየሱስ ጌታ ነህ (፪x)
አባቴ ጌታ ነህ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እንደማያልፍ የለም አለፈ በተራ (ጌታ እኮ ነህ (፪x))
እንደፈሳሽ ውኃ ያ ሁሉ መከራ (ጌታ እኮ ነህ (፪x))
በዚያ ክፉ ሌሊት ደርሰህ አሳረፍከኝ (ጌታ እኮ ነህ (፪x))
ባለውለታዬ አንተው ክበርልኝ (ጌታ እኮ ነህ (፪x))
አዝማች · Chorus
ካለመኖር ወደመኖር ታመጣለህ
ቃል ይውጣ እንጂ ምንተስኖህ ትሰራለህ
ኢየሱስ ጌታ ነህ (፪x)
አባቴ ጌታ ነህ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ለብዙ ዘመናት በዓልጋው ለነበረው (ጌታ እኮ ነህ (፪x))
ዘመን መጥቶለታል ለዚያ ለሽባው ሰው (ጌታ እኮ ነህ (፪x))
እስርአቱን ፈተህ አዘልለኸዋል (ጌታ እኮ ነህ (፪x))
አቤት የእኔ ጌታ ለአንተ ምን ይሳናል (ጌታ እኮ ነህ (፪x))
ጨለማ በፊቴ አይጨልምም
ጌታ ነህ ኢየሱስ ለዘለዓለም
እኔማ ኧረ እንዴት ዝም እላለሁ
ከሞት ያመለጥኩት በአንተ እኮ ነው
ጌታ የእኔ ማረፊያ ጌታ መታመኛዬ አዎ
ጌታ ስንቱን አለፍኩት ጌታ በአንተ ትምኜው
አዝማች · Chorus
ካለመኖር ወደመኖር ታመጣለህ
ቃል ይውጣ እንጂ ምንተስኖህ ትሰራለህ
ኢየሱስ ጌታ ነህ (፪x)
አባቴ ጌታ ነህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ