ዘመን መጣ
Zemen Meta
ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ገመዴ ባማረ ውብ ስፍራ ወደቀችልኝ (፪x)
እርስቴም በእርሱ በኢየሱሴ ተዋበችልኝ (፪x)
እፎይ አሰኘኝ ጌታ ቤቴ ገብት
መራራ የሆነውን ታሪኬን ለውጦ (፪x)
አዝማች · Chorus
መጐብኛዬ ዘመን መጣ
ቀን ወጣልኝ በዚህ ጌታ
አርፌያለሁ በዓለቱ ላይ
ሲደርስልኝ ጌታ ከላይ
ጌታ ከላይ ከላይ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በምድረበዳ ውስጥ ከአለት ውኃ አፍልቆ
እኔን አረካልኝ መገፋቴን አይቶ
የዘመናት ለቅሶ እምባ ታበሰልኝ
ልዑል ከዙፋኑ ለእኔ ሲነሳልኝ
ምሥጋና አሄ ምሥጋና አሄ አሄ
ምሥጋና አሄ ኢየሱስ ጌታዬ
አምልኮ አሄ አምልኮ አሄ አሄ
አምልኮ አሄ ለኢየሱስ ጌታዬ
ኢየሱስ ጌታዬ (፬x)
አዝማች · Chorus
መጐብኛዬ ዘመን መጣ
ቀን ወጣልኝ በዚህ ጌታ
አርፌያለሁ በዓለቱ ላይ
ሲደርስልኝ ጌታ ከላይ
ጌታ ከላይ ከላይ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መጐብኛዬ ጊዜው ዘመን መጥቶልኛል
የሃዘኑ ጊዜ አልፎ ደስታ ቤቴ ሞልቷል
ጠላት ዐይኑ እያየ ይሄው ጉብኝቴ
አከናወነልኝ ሁሉንም አባቴ
ምሥጋና አሄ ምሥጋና አሄ አሄ
ምሥጋና አሄ ኢየሱስ ጌታዬ
ዝማሬ አሄ ዝማሬ አሄ አሄ
ዝማሬ አሄ ለኢየሱስ ጌታዬ
ኢየሱስ ጌታዬ (፮x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ