የለህም እኩያ
Yelehem Ekuya
ትራክ 13 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሊታይ በማይቻል ብርሃን ውስጥ አለህ
ከምድር ጫፍ እስከጫፍ ሁሉ እኮ ግዛትህ
አለቅነት ስልጣን ክብር የአንተ ብቻ
እናመልክሃለን ኢየሱስ የለህ ብቻ (፪x)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ (፪x)
ሃሌሉያ የለህም እኩያ (፪x)
የለህም እኩያ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ስግደትና አምልኮ ለጌታ ለሰራዊት ሁሉ አለቃ
ለሆንከው አባታችን ንጉሣችን (ንጉሣችን)
ፈዋሻችን ነህ አዳኛችን ምርኩዛችን መታመኛችን
እርስታችን እግዚአብሔር ሃገራችን (ሃገራችን)
እንገዛልሃለን ወድቀን አዲስ ቅኔን እየተቀኘን
ክበር ለዘለዓለም ንገሥ ለዘለዓለም ቅዱስ አባታችን
ሰማይ ዙፋንህ ነው ምድር መረገጫህ
ጊዜና ሁኔታ ቦታ አይወስንህ
አሰራርህ ግሩም ከአይምሮ በላይ ነው
አገዛዝህ ምቹ ከማንም ልዩ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ (፪x)
ሃሌሉያ የለህም እኩያ (፪x)
የለህም እኩያ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ስግደትና አምልኮ ለጌታ ለሰራዊት ሁሉ አለቃ
ለሆንከው አባታችን ንጉሣችን (ንጉሣችን)
ፈዋሻችን ነህ አዳኛችን ምርኩዛችን መታመኛችን
እርስታችን እግዚአብሔር ሃገራችን (ሃገራችን)
እንገዛልሃለን ወድቀን አዲስ ቅኔን እየተቀኘን
ክበር ለዘለዓለም ንገሥ ለዘለዓለም ቅዱስ አባታችን
የጥበብ ሁሉ ምንጭ የዕውቀት መሰረት
የሰላም የደስታ የፍቅር ተምሳሌት
አንተ እኮ ነህ ጌታ ለእኛስ ማረፊያችን
እውነተኛ ወዳጅ ብሩኩ ተስፋችን (፪x)
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ (፪x)
ሃሌሉያ የለህም እኩያ (፪x)
የለህም እኩያ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ