ከሁሉ በላይ ነው
Kehulu Belay New
ትራክ 10 · 6:40 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነው
የእኔ ጌታ በዙፋኑ ላይ ነው
ማነው የሚመስለው እርሱ ኤልሻዳይ ነው
ማነው የሚያክለው እርሱ የበላይ ነው አዎ
አዝማች · Chorus
ከሁሉ በላይ ነው ጌታ
ከሁሉ በላይ በላይ
ከሁሉ በላይ ነው ኢየሱስ
ከሁሉ በላይ በላይ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በምድር ሁሉ ላይ ገነው የነበሩ
እጅግ የከበሩ ደግሞም የተፈሩ
ብርቱ ሃያላኖች ጠቢባን ወድቀዋል
ብዙዎች ነገሥታት ወድቀው ተረስተዋል
የእኛ ግን እግዚአብሔር ዛሬም ክንደ ብርቱ
ጉልበቱ ሳይደክም አለ በዙፋኑ በዙፋኑ
አለ በዙፋኑ አዎ
መቃብር ፈንቅሎ ድል ነስቶ የተነሳ
እርሱ ነው ኢየሱስ የይሁዳ አንበሳ (፪x)
የይሁዳ አንበሳ አዎ
አዝማች · Chorus
ከሁሉ በላይ ነው ጌታ
ከሁሉ በላይ በላይ
ከሁሉ በላይ ነው ኢየሱስ
ከሁሉ በላይ በላይ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ከሁሉ በላይ በላይ (፫x)
ናቡከደነጾር ምስል አሰራና
ስገዱ አላቸው አምላክ ነው አለና
ለምስሉ ከቶ አንሰግዱም ያሉ
እነሲድራቅ ታስረው በእቶኑ ተጣሉ
ሰባት እጥፍ ሆኖ ቢነድም እሳቱ
እርሱን የታመኑ አሸንፈው ወጡ ሃሌሉያ
ድል አድርገው ወጡ [1]
የነሲድራቅ አምላክ አሁንም ይሰራል
ስሙን ለሚጠራው ከሞትም ያድናል ሃሌሉያ
ከሞትም ያድናል አዎ
ኢየሱስ ጌታ ነው አሃ
ኢየሱስ ጌታ ጌታ
ኢየሱስ ጌታ ነው ኦሆ
ኢየሱስ ጌታ ጌታ (፪x)
ኢየሱስ ጌታ ጌታ (፫x)
በጸናችው እጁ ህዝቡን አወጣቸው [2]
ባሕሩን አሻግሮ በድንቅ መራቸው [3]
ከኋላም ከፊትም ሆኗቸው ከለላ
ተስፋውን ወረሱ ቃሉንም አጸና [4]
ለእኔማ አባቴ ነው ዛሬም አምነዋለሁ
ቢጐድልም ቢሞላም እግዚአብሔር ትልቅ ነው
በቁሳቁስ ነገር እኔ አልመዝነውም
ከሁሉም ይልቃል ጌታ እኩያ የለውም አባብዬ
እኩያ የለውም አዎ
አዝማች · Chorus
ከሁሉ በላይ ነው ጌታ
ከሁሉ በላይ በላይ
ከሁሉ በላይ ነው ኢየሱስ
ከሁሉ በላይ በላይ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከሁሉ በላይ በላይ (፫x)
እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነው (በዙፋኑ ላይ)
የእኔ ጌታ በዙፋኑ ላይ ነው (ኦ ላይ ነው)
ማነው የሚመስለው (የእኔ ጌታ) እርሱ ኤልሻዳይ ነው (ማነው ማነው)
ማነው የሚያክለው (ኢየሱሴን) እርሱ የበላይ ነው (አዎ አዎ)
ቁጥር 5 · Verse 5
ከሁሉ በላይ ነው ጌታ (በላይ በላይ)
ቁጥር 6 · Verse 6
ከሁሉ በላይ በላይ (በላይ ነው)
ከሁሉ በላይ ነው ኢየሱስ (በላይ በላይ)
ከሁሉ በላይ በላይ (፪x)
ከሁሉ በላይ በላይ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ