Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ወዶኛል እና አዳነኝ

Wedognal Ena Adanegn

ትራክ 7 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቸርነቱን ለእኔ ሁሌ እዘምራለሁ

የአባትነት ፍቅሩን ቀምሼ ስላየሁ

ጐልጐታ አናት ላይ ለእኔ ሞቶልኛል

የኀጢአት እስራቴን በጥሶ ጥሎታል (፪x)

ወዶኛልና አዳነኝ (፪x)

ምህረቱ ሰው አደረገኝ (፫x)

ወዶኛልና አዳነኝ (፪x)

ምህረቱ ሰው አደረገኝ (፫x)

ከሰማይ ሰማያት ከዙፋኑ ወርዶ

ሁሉን ስለፍቅር አደረገ ባዶ

መስቀል ተሸክሞ ደፋ ቀና ያለው

ያ ሁሉ ስቃዩ ለእኔ ነው ለእኔ ነው (፪x)

ወዶኛልና አዳነኝ (፪x)

ምህረቱ ሰው አደረገኝ (፫x)

አደባባይ ቆመ እርቃኑን ስለ እኔ

አላፈረብኝም ኢየሱስ መድኅኔ

በእኔ ፈንታ ሞቶ እኔን አድኖኛል

በከበረው ደሙ ጌታዬ ዋጅቶኛል (፪x)

ወዶኛልና አዳነኝ (፪x)

ምህረቱ ሰው አደረገኝ (፫x)

የምህረት መግቢያ በሩ ተክፈተ

የጥሉ ግድግዳ በደሙ ፈረሰ

ተፈጸመ ብሎ ሁሉን ጨርሶታል

ሞትና ሲዖልን ድል ነስቶ ተነስቷል (፪x)

ወዶኛልና አዳነኝ (፪x)

ምህረቱ ሰው አደረገኝ (፮x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ