በአንተ ደስ ይለኛል
Beante Des Yelegnal
ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጉድለቴን ሸፍነህ እዚህ አደረስከኝ
ያን ሁሉ ሸለቆ አዝለህ ያሻገርከኝ
ኢየሱሴ ተባረክልኝ (፪x)
አባብዬ ተባረክልኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ማዳን በማይችሉት እኔስ አልመካም
አንተ ብቻ እኮ ነህ የሕይወቴ ጌታ
አንተ ነህ (፪x) አንተ እኮ ጌታ
አንተ ነህ (፪x) አንተ እኮ ጌታ
አንተ እኮ ጌታ (፪x) ፤ አንተ ብቻ ጌታ (፪x)
ከንጉሥ ገበታ የማይገባኝን (፪x)
ሁሉ በድካሜ የተጸየፈኝን (፪x)
ከማዕድን መሃል አስቀምጠኸኛል (፪x)
ኦ ኢየሱሴ ፍቅርህ እኔን ሰው አድርጐኛል ፤ ምን ብል ያረካኛል
ተባረክልኝ (፫x) አባቴ ተባረክልኝ
ከፍ በልልኝ (፫x) ኢየሱሴ ከፍ በልልኝ
አዝማች · Chorus
ጉድለቴን ሸፍነህ እዚህ አደረስከኝ
ያን ሁሉ ሸለቆ አዝለህ ያሻገርከኝ
ኢየሱሴ ተባረክልኝ (፪x)
አባብዬ ተባረክልኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተራራ ስወጣ ጉልበት እየሆንከኝ (፪x)
ስወድቅ ስነሳ እየደጋገፍከኝ (፪x)
አቤት በአንተ ብርታት ስንቱን አልፌያለሁ (፪x)
በምህረትህ ብዛት እዚህ ደርሻለሁ ፤ ዛሬ ደርሻለሁ
ተባረክልኝ (፫x) አባቴ ተባረክልኝ
ከፍ በልልኝ (፫x) ኢየሱሴ ከፍ በልልኝ
ትላንትን አልፌ እዚህ እኮ መድረሴ
በአንተ ብርታት እንጂ አይደለም በራሴ (፪x)
ትላንትን አልፌ እዚህ እኮ መድረሴ
በአንተ ብርታት እንጂ አይደለም በራሴ (፪x)
አይደለም በራሴ በራሴ አይደለም በራሴ (፪x)
አዝማች · Chorus
ጉድለቴን ሸፍነህ እዚህ አደረስከኝ
ያን ሁሉ ሸለቆ አዝለህ ያሻገርከኝ
ኢየሱሴ ተባረክልኝ (፪x)
አባብዬ ተባረክልኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ