ስንቱን ላውራ
Sentun Lawra
ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በመከራዬ ቀን ላልተለየኝ
አበሳዬን ከኔ ላራቀልኝ
ለዚህ ለጌታዬ እሰግዳለሁ
ሁልጊዜ ምሥጋናን አበዛለሁ
ዘምርለታለሁ (፭x) ለአባቴ ዘምርለታለሁ
አዝማች · Chorus
ስንቱን ላውራው ልተርከው
አንተ ያደረከው ከአይምሮ በላይ ነው ጌታ
ከአይምሮ በላይ ነው (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ፊትለፊት ቆሞ ከፍ ያለ ተራራ
የመድሃኒቴ አምላክ ስልህ ሰማኸኝ ስጣራ
በተራራዬ ላይ በድል አራመድከኝ
ከሳሶቼ እያዩ አሜን ተስፋዬን ወረስኩኝ
ተስፋዬን ሰበርኩት
አዝማች · Chorus
ስንቱን ላውራው ልተርከው
አንተ ያደረከው ከአይምሮ በላይ ነው ጌታ
ከአይምሮ በላይ ነው (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ተስፋዬን ቆርጬ ለሰው ያልነገርኩት
አበቃለት ብዬ ሞቶ የቀበርኩት
ምንተስኖህ ጌታ ሁሉ ተችሎሃል
አንገት ያስደፋኝን ቀንበሬን ሰብረሃል ጌታ
ቀንበሬን ሰብረሃል
አዝማች · Chorus
ስንቱን ላውራው ልተርከው
አንተ ያደረከው ከአይምሮ በላይ ነው ጌታ
ከአይምሮ በላይ ነው (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አዋጅ ሲል ጠላቴ እኔን ሊያጠፋ
ከበሮ ሲያስደልቅ ነጋሪት ሲያስመታ
በአንድ ሌሊት ጀምበር ታሪክ ተቀየረ
ጠላት በቆፈረው አሜን ጉድጓድ ተቀበረ እሰይ
ጉድጓድ ተቀበረ
በመከራዬ ቀን ላልተለየኝ (ላልተለየኝ)
አበሳዬን ከኔ ላራቀልኝ (ላራቀልኝ)
ለዚህ ለጌታዬ እሰግዳለሁ
ሁልጊዜ ምሥጋናን አበዛለሁ ዘምርለታለሁ አዎ
ዘምርለታለሁ (ዘምርለታለሁ) (፪x)
ዘምርለታለሁ ለአባቴ ዘምርለታለሁ (አቤት አቤት)
ቁጥር 5 · Verse 5
ስንቱን ላውራ (ላውራ) ልተርከው (ልተርከው)
ቁጥር 6 · Verse 6
አንተ ያደረከው (ያደረከው)
ከአይምሮ በላይ ነው ጌታ (በላይ በላይ ነው)
ከአይምሮ በላይ ነው (፬x) (በላይ በላይ)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ