Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንዳንተ ያለ

Endante Yale

ትራክ 9 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንዳንተ ያለ (፫x) አባቴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ

እንዳንተ ያለ (፫x) ኢየሱሴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ

ኦ መዳኔ እጅግ ይደንቀኛል

የፍቅርህ ብዛቱ እንዲህ ያዘምረኛል

ውለታህ መች ዝም ያሰኛል (፫x)

ላውራ ማዳንህን ጌታ

ላውራ ስራህን ኢየሱስ (፪x)

ተስፋ ቆርጬ ሌት ቀን ሳነባ

መድረሻ ጠፍቶኝ ሆኜ እምባ በእምባ

እንዳንተ ማነው የደረሰልኝ

እምባዬን ጠርጐ ና ልጄ ሆይ ያለኝ

እንዳንተ ያለ (፫x) አባቴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ

እንዳንተ ያለ (፫x) ኢየሱሴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ

ጐልያድ በፊቴ እንዲያው ተደንቅሮ

ባስጨነቀኝ ቁጥር ሳሰማ እሮሮ

ኧረ እንዳንተ ማነው ከተፍ ያለልኝ

ያንን ተራራውን ከፊቴ ጣለልኝ

እንዳንተ ያለ (፫x) አባቴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ

እንዳንተ ያለ (፫x) ኢየሱሴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ

በጨነቀኝ ጊዜ ጌታ አንተን ጠራሁህ

መታመኛዬ ሆይ ወዴት ነህ አልኩህ

አንተም አልናከኝም ቃሌን ሁሉ ሰማህ

ምሥጋና ውዳሴ ክብር ይሁንልህ

እንዳንተ ያለ (፫x) አባቴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ

እንዳንተ ያለ (፫x) ኢየሱሴ ለእኔስ ከቶ ማን አለ

ኦ መዳኔ እጅግ ይደንቀኛል

የፍቅርህ ብዛቱ እንዲህ ያዘምረኛል

ውለታህ መች ዝም ያሰኛል (፫x)

ላውራ ማዳንህን ጌታ

ላውራ ስራህን ኢየሱስ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ