ሁሉ በእርሱ ሆነልኝ
Hulu Bersu Honelegn
ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሁሉ በእርሱ ሆነልኝ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደ ጠላቴ/ከሳሼ አልሆነብኝም
ጌታ አሸነፈልኝ ሃሌሉያ (፪x)
ተሻገርኩኝ (፪x) አቅፎ ደግፎ አሻገረኝ
እጄን ይዞኝ ጌታ እጄን ይዞኝ አዎ
እጄን ይዞኝ ኢየሱስ እጄን ይዞኝ አዎ
የማደርገው መላ ቢጠፋብኝ
በሬን ዘጋሁ ጊታ ብዬ ጮህኩኝ
ድንገት መጥቶ ሰላም ይሁን ብሎ
አበሳዬን ከላይ አንከባሎ ፤ አሳረፈኝ (፫x)
ይሄ ነው ጌታ እስራቴን የፈታ
ይሄ ነው ጌታ ሰንሰለቴን የፈታ
አዝማች · Chorus
ሁሉ በእርሱ ሆነልኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እንደ ከሳሼ አልሆነብኝም
ጌታ አሸነፈልኝ ሃሌሉያ
ተሻገርኩኝ (፪x) አቅፎ ደግፎ አሻገረኝ
እጄን ይዞኝ ጌታ እጄን ይዞኝ አዎ
እጄን ይዞኝ ኢየሱስ እጄን ይዞኝ አዎ
ጽኑ ቅጥር ዙሪያቸውን ቀጥረው
እንዳላልፍ በመንገዴ ቆመው
አላስገባም ያሉኝ ጠላቶቼ
በአንዴ ጩኸት ወደቁ ከእግሮቼ
አዩ ዐይኖቼ (፫x)
ይሄ ነው ጌታ ጠላቶቼን የመታ
ይሄ ነው ኢየሱስ ከሳሾቼን የመታ
አዝማች · Chorus
ሁሉ በእርሱ ሆነልኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እንደ ከሳሼ አልሆነብኝም
ጌታ አሸነፈልኝ ሃሌሉያ
ተሻገርኩኝ (፪x) አቅፎ ደግፎ አሻገረኝ
እጄን ይዞኝ ጌታ እጄን ይዞኝ አዎ
እጄን ይዞኝ ኢየሱስ እጄን ይዞኝ አዎ
ያጠላቴ ጦሩን ሰበቀብኝ
ከግድግዳ ጋራ ሊያጣብቀኝ
ቀስቱን ሁሉ ሰባበረውና
አስመለጠኝ ጋሻ ሆነኝና
ኢየሱስ ገናና (፫x)
ይሄ ነው ጌታ ጠላቶቼን የመታ
ይሄ ነው ጌታ ከሳሾቼን የመታ
አዝማች · Chorus
ሁሉ በእርሱ ሆነልኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እንደ ከሳሼ አልሆነብኝም
ጌታ አሸነፈልኝ ሃሌሉያ
ተሻገርኩኝ (፪x) አቅፎ ደግፎ አሻገረኝ
እጄን ይዞኝ ጌታ እጄን ይዞኝ አዎ
እጄን ይዞኝ ኢየሱስ እጄን ይዞኝ አዎ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ