አላማዬ ነው
Alamayie New
ትራክ 2 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር አላማዬ ነዉ (፪x)
ጠላት የሚለኝን ለምንስ ልስማዉ
ልውጣ ልሄድ ልውረሰዉ አዎ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
አላማ ያላቸው የጥንት አባቶቼ
ድል አደረጉ እንጂ ተሸነፉ መቼ
እኔም አላማዬን አንተን አድርጌያለሁ
የጠላቶቼን ደጅ በእምነት እወርሳለሁ
እወርሳለሁ ፤ እወርሳለሁ (፬x)
አማሌቅ በፊቴ ሆኖ ቢያቅራራ
ምን ትልቅ ቢመስል እኔ እንደው አልፈራ
የአምላኬን ስም ይዤ በእምነት እወጣለሁ
ጠላቴን ከእግሬ ስር አጋድመዋለሁ
አምላኬ ሃይሌ ነው
እኔ አልፈራም አልፈራም (፪x)
እኔ አልሰጋም አልሰጋም (፪x)
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር አላማዬ ነዉ (፪x)
ጠላት የሚለኝን ለምንስ ልስማዉ
ልውጣ ልሄድ ልውረሰዉ አዎ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እንደ ሰናኦር ግምብ ቢቆምም በፊቴ
ይደባልቀዋል ቋንቋውን አባቴ
ምርኮን በምርኮ ላይ ይጨምርልኛል
ያመንኩት ጌታዬ መቼ ይተወኛል (፪x)
እኔ አልፈራም አልፈራም (፪x)
እኔ አልሰጋም አልሰጋም (፪x)
የድል ሰንደቄ ነው የሕይወቴ አርባ አሃሃ
እኔ የማመልከው ጌታ ባለግርማ
ባለግርማ ኢየሱስ ባለግርማ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ