አልፋ ኦሜጋ
Alpha Omega
ትራክ 10 · 3:26 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የለውም ወሰን ለኃይሉ ማብቂያ
የፍጥረት በኩር የመጀመሪያ
ዘለዓለማዊ ሕያው እግዚአብሔር
አሁንም ወደ ፊት ያለ የሚኖር
ቁጥር 2 · Verse 2
አልፋ ኦሜጋ (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አልፋ ኦሜጋ ነው ጌታ
አልፋ ኦሜጋ ነው ኢየሱስ (፪x)
ወርድ ስፋቱ ርዝመት ጥልቀቱ
ክብርና ኃይሉ አምላክነቱ
በሰማይ በምድር ላለው ችሎቱ
ተቆጣጣሪ የለውም ብርቱ
አዝማች · Chorus
አልፋ ኦሜጋ ነው ጌታ
አልፋ ኦሜጋ ነው ኢየሱስ
አልፋ ኦሜጋ ነው ጌታ
አልፋ ኦሜጋ ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ዘላቂ ሰላም የሰው ልጅ ተስፋ
ሥሙ እግዚአብሔር አልፋ ኦሜጋ
የደካማው ኃይል የብርቱ መሪ
ከዘመን ዘመን አሸጋጋሪ
አዝማች · Chorus
አልፋ ኦሜጋ ነው ጌታ
አልፋ ኦሜጋ ነው ኢየሱስ
አልፋ ኦሜጋ ነው ጌታ
አልፋ ኦሜጋ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ