Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንደገና

Endegena

ትራክ 7 · 5:49 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንደገና (፪x)

በአንድነት ሰብስቦ ላቆመን ሆ

ክበር ይሁን (፪x)

ለአምላካችን እዚህ ላደረሰን

እንደገና (እንደገና) (፪x)

በአንድነት ሰብስቦ ላቆመን ሆ

ክበር ይሁን (አሜን ይሁን)

ክበር ይሁን (ለእርሱ ይሁን)

ለአምላካችን እዚህ ላደረሰን

ባገኘን መከራ እረድቶ

በድካም በብርታት ተመልክቶ

እስካሁን ጠብቆ አድርሶናል

ክብር ይገባዋል

እንደገና (እንደገና) (፪x)

በአንድነት ሰብስቦ ላቆመን ሆ

ክበር ይሁን (አሜን ይሁን)

ክበር ይሁን (ለእርሱ ይሁን)

ለአምላካችን እዚህ ላደረሰን (፪x)

ጠላት መጥፊያችንን ተመኝቶ

በአንድነታችን ላይ ነጋሪት ፈፅሞ

የማይታክት አምላክ ታድጐናል

ክብር ይገባዋል

እንደገና (እንደገና) (፪x)

በአንድነት ሰብስቦ ላቆመን ሆ

ክበር ይሁን (አሜን ይሁን)

ክበር ይሁን (ለእርሱ ይሁን)

ለአምላካችን እዚህ ላደረሰን (፪x)

እንደ ሳር ጠውልገን በደረቅን ጊዜ

ዝለን ተደካክመን ስንሄድ በተካዜ

አቅፎና ደግፎ አቁሞናል

ክበር ይገባዋል

እንደገና (እንደገና) (፪x)

በአንድነት ሰብስቦ ላቆመን ሆ

ክበር ይሁን (አሜን ይሁን)

ክበር ይሁን (ለእርሱ ይሁን)

ለአምላካችን እዚህ ላደረሰን (፪x)

አሁንም አሁንም እንደገና

ለአምላካችን ይድረሰው ምሥጋና

በምህረቱ ዛሬ አድርሶናል

ክብር ይገባዋል

እንደገና (እንደገና) (፪x)

በአንድነት ሰብስቦ ላቆመን ሆ

ክበር ይሁን (አሜን ይሁን)

ክበር ይሁን (ለእርሱ ይሁን)

ለአምላካችን እዚህ ላደረሰን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ