Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነው

Egziabhier Bezufanu Lay New

ትራክ 3 · 4:41 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነው (፫x)

ማን ነው የሚረታው (፪x)

ብዙዎች ተነሱ ከእርሱ ጋር ሊገጥሙ

መች ተሳካላቸው ተንኮታኩተው ቀሩ

ዛሬም በዙፋኑ ተንሰራፍቶ ይኖራል

ኃይለኛው እግዚአብሔርን ማንስ ይረታዋል ?

እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነው (፫x)

ማን ነው የሚረታው (፪x)

ጐልያድን በድፍረት በእርሱ ላይ ተነስቶ

ተገዳድሮት ነበር ጡንቻውን ተማምኖ [1]

በዙፋኑ ያለው እግዚአብሔር ጌታ ነው

ተዘርሮ ቀረ ጌታዬ አሸነፈው [2]

እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነው (፫x)

ማን ነው የሚረታው (፪x)

ዕቅዱን እንዳይፈፅም ማነው የሚያግደው

ድንቅን እንዳይሰራ ማንስ ተቋቋመው

ሁሉን የሚረታ የነገሥታት ንጉሥ ነው

ዛሬም በዚህ ዘመን ጌታችን ጌታ ነው

እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነው (፫x)

ማን ነው የሚረታው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ