Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው

Ende Egziabhier Yale Manew

ትራክ 12 · 6:05 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው

ተስፋ በሌለበት ጭልምልም ባለበት

ስሜትን አዋቂ በልብም ዘላቂ (፪x)

የጠላቴ ሰልፍ በርትቶብኝ

ስፍራዬን እስክለቅ አስጨንቆኝ

በክንፎቹ ጥላ ጋረደኝ

ጋሻ ረድኤቴ እግዚአብሔር ሆነልኝ

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው

ተስፋ በሌለበት ጭልምልም ባለበት

ስሜትን አዋቂ በልብም ዘላቂ (፪x)

በጨካኞች ቁጣ አስትንፋስ

ህዝብህን በሚመታ አውሎ ነፍስ

በችግሬ በጭንቄ ሰዓት

መመኪያዬ እፎይ ያልኩበት

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው

ተስፋ በሌለበት ጭልምልም ባለበት

ስሜትን አዋቂ በልብም ዘላቂ (፪x)

ሀዘን ጭንቀት እጅግ በዝቶብኝ

መራመድ አቅቶኝ ጨልሞብኝ

እግዚአብሔር ሆነ ብርሃኔ

ላመስግነው በአዲስ ቅኔ

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው

ተስፋ በሌለበት ጭልምልም ባለበት

ስሜትን አዋቂ በልብም ዘላቂ (፪x)

የልቤ አምላክ እርሱ ታላቅ ነው

በማግኘት በማጣቴ የማመልከው

ሆኖልኛል ለፀሎቴ መልስ

አክብረዋለሁ በእኔ እንዲነግሥ

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው

ተስፋ በሌለበት ጭልምልም ባለበት

ስሜትን አዋቂ በልብም ዘላቂ (፪x)

ምሥጋናው ምድርን የሞላ

የፍጥረታት ገዢ የለም ሌላ

በጥበቡ አቻ የሌለው

አልፋ ኦሜጋ አምላካችን ነው

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው

ተስፋ በሌለበት ጭልምልም ባለበት

ስሜትን አዋቂ በልብም ዘላቂ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ