Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እርሱ እግዚአብሔር ነውና

Ersu Egziabhier Newena

ትራክ 2 · 4:45 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

እርሱ እግዚአብሔር ነውና

ደስ የሚያሰኘውን ያድርገው እያልን (፪x)

ዕቅዱ ያማረ ሀሳቡ የቀና

አለ ፈጣሪያችን ከቶ ማን አለና

ለእርሱ እናስረክበው

የወደደውን ያድርገው (፪x)

እርሱ እግዚአብሔር ነውና

ደስ የሚያሰኘውን ያድርገው እያልን (፪x)

ሰው ለሥጋው ብቻ በጐውን ያደርጋል

የሚያጠፋውን ሁሉ መልካም ብሎ ያስባል

ከንቱ ነው ከንቱ ነው

ሰውስ የሚያስበው (፪x)

እርሱ እግዚአብሔር ነውና

ደስ የሚያሰኘውን ያድርገው እያልን (፪x)

ሁሉን የሚያውቅ ጌታ መልካሙን ያደርጋል

የወደድነውን ሁሉ በደሙ አድሶናል

መልካም ነው ዓላማው

ይሥራ እንደ ወደደው (፪x)

እርሱ እግዚአብሔር ነውና

ደስ የሚያሰኘውን ያድርገው እያልን (፪x)

እግዚአብሔር ኃያል ነው ሥራው ያማረ ነው

እስቲ ለእርሱ እንስጠው ሁሉን ይፈፅመው

እናያለን ለውጥን

ያማረ መሆኑን (፪x)

እርሱ እግዚአብሔር ነውና

ደስ የሚያሰኘውን ያድርገው እያልን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ