Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ብሩክ ይሁን

Beruk Yehun

ትራክ 11 · 2:40 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የዘለዓለም እግዚአብሔር የቅዱሳን መታመኛ

በትካዜ በመከራ መጠለያ ነው መፅናኛ

ቅዱስ አምላክ የዘላለም

የሚመስለው ፍፁም የለም (፪x)

ብሩክ ይሁን የእግዚአብሔር ሥም

ብሩክ ይሁን አሜን (፪x)

ልምላሜም በረከት ከእርሱ በሚሆን ደስታ

አፍሶልናል እግዚአብሔር ዘለዓለማዊን እርካታ

ምርጫችን አምላካችን ነው

ያዋጣናል ብለን የያዝነው (፪x)

ብሩክ ይሁን የእግዚአብሔር ሥም

ብሩክ ይሁን አሜን (፪x)

አደራን በመጠበቁ ፍፁም ሆኖ የታመነ

መንፈስ ነፍስና ሥጋ ያለ ነውር የጠበቀ

ከእኛ ጋር ሆኖ እስካሁን

ጠብቆናል በሕይወታችን (፪x)

ብሩክ ይሁን የእግዚአብሔር ሥም

ብሩክ ይሁን አሜን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ