Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አሜን ሁሉን ትችላለህ

Amien Hulun Techelaleh

ትራክ 6 · 5:20 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አሜን ሁሉን ትችላለህ

አሜን ሁሉን ታደርጋለህ

የለም የሚያቅትህ (፪x)

በሰማይ በምድር ሥልጣን ነው በእጅህ

ከአቅምህ በላይ ሆኖ የለም የሚያቅትህ

ዕቅድ ስታደርግ ሀሳብህን ስትፈፅም

ከቶ ማን ይችላል ፈቃድህን ሊቋቋም

አሜን ሁሉን ትችላለህ

አሜን ሁሉን ታደርጋለህ

የለም የሚያቅትህ (፪x)

ተስፋ ለቆረጠ ተስፋ ትሆናለህ

በሞተ ሕይወት ውስጥ ነፍስን ተዘራለህ

የቆሰለውንም ትፈውሰዋለህ

በምድር በሰማይ ሁሉን ቻይ ጌታ ነህ

አሜን ሁሉን ትችላለህ

አሜን ሁሉን ታደርጋለህ

የለም የሚያቅትህ (፪x)

ብዙ ወጥተን ወርደን መልስ ላጣንለት

ተጨንቀን ተጠበን ለጐሰቆልንበት

ድምፅህን ስትልክ ታበጃጀዋለህ

ለችግሮቻችን መፍትሄው አንተ ነው

አሜን ሁሉን ትችላለህ

አሜን ሁሉን ታደርጋለህ

የለም የሚያቅትህ (፪x)

በቅዱሳንህ ላይ አላማህ ፍቅር ነው

ሀሳብህ ጥልቅ ነው ማንም አይችል ሊያውቀው

በክፉ በመልካም ተስኬዳቸዋለህ

በቃልህ ማንሳትን ትችልበታለህ

አሜን ሁሉን ትችላለህ

አሜን ሁሉን ታደርጋለህ

የለም የሚያቅትህ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ