Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሰላም አለ በኢየሱስ

Selam Ale Beyesus

ትራክ 1 · 6:00 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሰላም (፪x) አለ በኢየሱስ

እረፍት (፪x) አለ በኢየሱስ

ያልቀመስከው ክብር ዝና እየው (፪x)

የመዳን ቀን ዛሬ ነው አይለፍብህ

ጌታህን ተገናኝ ለፍርድ ሳይመጣብህ

በማሾፍ ከምታሳልፍ ወርቃማውን ጊዜህ

ቅመሰው ኢየሱስን ወንድሜ እባክህ

ሰላም (፪x) አለ በኢየሱስ

እረፍት (፪x) አለ በኢየሱስ

ያልቀመስከው ክብር ዝና እየው

በእጅህ ለመዳሰስ ሳትፈልግ ሳታምፅ

በእምነት ቅረብ ወደሱ አውርድ ሸክምህን

የፍርድ አምላክ መሆኑን ወንድሜ አትዘንጋ

ለሰው ልጅ ሁሉ ሲል ሕይወቱን የሰዋ

ሰላም (፪x) አለ በኢየሱስ

እረፍት (፪x) አለ በኢየሱስ

ያልቀመስከው ክብር ዝና እየው

ሰላምን ለማግኘት ከምድር መች ሆነ

ሰላም የሆነ ኢየሱስ በውስጥ ካልሰመነ

ደስታ ለማግኘት ብዙ አትባክን

በሞኝነት መጥተህ ኢየሱስን እመን

ሰላም (፪x) አለ በኢየሱስ

እረፍት (፪x) አለ በኢየሱስ

ያልቀመስከው ክብር ዝና እየው

ደስታን በዘፈን ሁሉን ሞክረሃል

እርካታን ለማግኘት ብዙ ተሯሩጠሃል

የመዳን ቀን ሳያልፍ ቀኑ ሳይጨልም

ሰላምን ለማግኘት በኢየሱስ መታመን

ሰላም (፪x) አለ በኢየሱስ

እረፍት (፪x) አለ በኢየሱስ

ያልቀመስከው ክብር ዝና እየው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ