ምሥጋና ለአዳኛችን
Mesgana Ladagnachen
ትራክ 9 · 4:20 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ለአዳኛችን ምሥጋና
ምሥጋና ለተቤዥን ምሥጋና
ምሥጋና ዛሬም ነገም ገናና
ለሆነው ኢየሱስ ነውና (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌታችንን እናክብር በአንድነት
ለሠራው ድንቅ ኑ እንስገድለት
እናመስግን በአፋችን ዝማሬ
የምሥጋና የድል ቀን ነው ዛሬ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ለአዳኛችን ምሥጋና
ምሥጋና ለተቤዥን ምሥጋና
ምሥጋና ዛሬም ነገም ገናና
ለሆነው ኢየሱስ ነውና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በአዲስ ቅኔ አመስግኑት ጌታን
እጅግ ብዙ ብዙ ነው ችሎታው
ኦ ኢየሱስ ክብሩ ሁሉ ገነነ
ጠላታችን ሥራው ተዳፈነ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ለአዳኛችን ምሥጋና
ምሥጋና ለተቤዥን ምሥጋና
ምሥጋና ዛሬም ነገም ገናና
ለሆነው ኢየሱስ ነውና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ ይክበር መታው ጠላታችን
በኢየሱስ ወድቋል ከሥራችን
በምሥጋና የከበረ ዜማ
በሰማይ ሰማያት ይሰማ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ለአዳኛችን ምሥጋና
ምሥጋና ለተቤዥን ምሥጋና
ምሥጋና ዛሬም ነገም ገናና
ለሆነው ኢየሱስ ነውና (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የዘለዓለም ባለውለታ ነው
ከሰይጣን ኃይል ያዳነኝ ጀግና ነው
በዕልልታ እንዘምር በደስታ
አለኝታችን ክብራችን ነው ጌታ
አዝማች · Chorus
ምሥጋና ለአዳኛችን ምሥጋና
ምሥጋና ለተቤዥን ምሥጋና
ምሥጋና ዛሬም ነገም ገናና
ለሆነው ኢየሱስ ነውና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ