Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ቸርነቱን ምህረቱን

Cherenetun Meheretun

ትራክ 8 · 5:23 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቸርነቱን ምህረቱን ከእኔ ላይ አላራቀም

የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ (፪x)

ገደላ ገደሉን ሸለቆ ስምጥ ዋሻ አስፈሪው

በሰው የማይደፈረውን በአምላኬ አልፌው

ዓይኔን የማነሳበት አንዳች ተስፋ ሳይኖረኝ

ሰማሁ የጌታዬን ድምፅ አለሁ ሲለኝ ሊረዳኝ

ቸርነቱን ምህረቱን ከእኔ ላይ አላራቀም

የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ (፪x)

በምድር እንደ ተፈጠረ መልካም ፍሬ እንዲያፈራ

ሊያይ ሲናፍቅ ጌታ ፍሬው ሁሉ ሲጐመራ

በሕይወት መሆኔ ቀርቶ የሞት ሸታ ሆኜ አገኘኝ

ጌታዬ ግን በምህረቱ ዳግም ለክብሩ አቆመኝ

ቸርነቱን ምህረቱን ከእኔ ላይ አላራቀም

የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ (፪x)

የድልን ተስፋ አያለሁ ምህረት ከጌታ ዘንድ ነው

የከበበኝን ጠላት ዳግም በዓይኔ ላላየው

ምህረቱ ለእኔ በዝቶ ክብሩን ላወራ ችያለሁ

የቸርነቱ ተካፋይ ሆኜ እኔም ስላየሁ

ቸርነቱን ምህረቱን ከእኔ ላይ አላራቀም

የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ