Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጌታ ሆይ

Gieta Hoy

ትራክ 4 · 4:21 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጌታ ሆይ ክንድህን ስናይ ብርታትህን ስናይ

ድል እናገኛለን በጠላታችን ላይ

ጌታ ሆይ ምህረትህን ስናይ ክብርህን ስናይ

ልባችን ይሞላል በደስታ ከላይ

ጌታ ሆይ ፈውስህን ስናይ ማዳንህን ስናይ

እምነት ይሞላናል በጉዞአችን ላይ

ጌታ ሆይ ክብርህን ስናይ ግርማህን ስናይ

ፍርሃት ይሞላናል የመንፈስ ቅዱስ ኃይል

ጌታ ሆይ ገድልህን ስናይ ሥራህን ስናይ

እናደንቅሃለን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል

ጌታ ሆይ ግርማህ ሲያበራ ሥራህ ሲጐላ

ነፍሳችን በሀሴት በደስታ ተሞላ

ጌታ ሆይ ቃልህ ሲባርከን ፀጋህ ሲያቆመን

ተመሥገን ለማለት ታላቅ ኃይል አገኘን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ